#Ethiopia | የ2026 ሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ አሸናፊዋ ሩታ ይርጋለም፣ ከ130 በላይ አገራት ተወዳዳሪዎች በሚሳተፉበት ዓለም አቀፍ የቁንጅና ውድድር ላይ ኢትዮጵያን በኩራት ለመወከል ቬትናም ደርሳለች።
ይህ ታላቅ መድረክ የሀገራችንን ባህል፣ ታሪክ፣ ጥበብና የቱሪዝም ሀብቶች ለዓለም ለማስተዋወቅ እንዲሁም የኢትዮጵያን አዎንታዊ ገጽታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማጎልበት ትልቅ አጋጣሚ እንደሆነ ተገልጿል።
”Beauty with Purpose” (ውበት ከዓላማ ጋር) በሚለው የመድረኩ መርህ መሠረት፣ ሩታ የኢትዮጵያን ውበትና ማንነት በብቃት ለማስተዋወቅ ዝግጅቷን አጠናቃለች።
የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ እና የፎከስ ስቱዲዮ (Focus Studio) ፕሮዳክሽን፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ሚዲያዎች፣ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እንዲሁም ሙሉ የኢትዮጵያ ወዳጆች በድምፅ መስጠት (Social Media Vote) እና መረጃዎችን በማሰራጨት ከሩታ ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።
እያንዳንዱ ድምፅ የኢትዮጵያ ድምፅ ነው!
ሩታ ለኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያ ከሩታ ጋር!
#MissWorld2026 #MissWorldEthiopia #RutaYirgalem #Ethiopia #Vietnam #FocusStudio
Source: GetuTemesgen









No comments yet.