ኢራን አሜሪካን መምታት የሚችሉ ሚሳኤሎችን እያዘጋጀች መሆኗን ገለጸች
አንድ ከፍተኛ የኢራን የሃይማኖት መሪ አገራቸው የሜሳይሎቿን የመምታት አቅም እስከ 15 ሺህ ኪሎ ሜትር ለማሳደግ በከፍተኛ ሁኔታ እየሰራች መሆኑንና ይህም አሜሪካን ቀጥታ ለመምታት ያስችላታል ሲሉ በይፋ ተናግረዋል።
የአህቫዝ ከተማ የጁምአ ሶላት መሪ አብዶልነቢ ሙሳቪፋርድ በሰጡት ይፋዊ መግለጫ አሜሪካውያንም በሚሳኤል መመታት እና በደም እንዲሁም በውድመት ውስጥ መወደቅ ምን እንደሚመስል እንዲረዱትና እንዲቀምሱት በሚል ኢራን ይህንን ረጅም ርቀት ተኳሽ ሚሳኤል እያዘጋጀች መሆኑን አስታውቀዋል።
ይህ መግለጫ በአይራን ኢንተርናሽናል የተዘገበ ሲሆን፣ የኢራን ባለስልጣናት ቀደም ሲል የነበራቸውን የ2 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚሳኤል ርቀት ገደብ ለማንሳት እና አህጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳኤሎችን ለማልማት እያደረጉት ያለውን ዝግጅት የሚያሳይ ነው ተብሏል።
ሆኖም ግን የወታደራዊና የደህንነት ባለሙያዎች እንደሚያስረዱት፣ ይህ የኢራን ባለስልጣን የተናገሩት ቃል የፖለቲካ ማስፈራሪያ እንጂ አገሪቱ በአሁኑ ወቅት አሜሪካን መሬት ድረስ መምታት የሚችል 15 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚጓዝ ሚሳኤል የላትም።
የኢራን የጦር መሳሪያዎች በአሁኑ ወቅት የሚደርሱት ከ2 ሺህ እስከ 3 ሺህ ኪሎ ሜትር ብቻ በመሆኑ፣ አቅሟ በመካከለኛው ምስራቅ እና በከፊል አውሮፓ ክልሎች ላይ ብቻ የተገደበ ነው።
ምንም እንኳን ኢራን ለሳተላይት ማሰወንጨፊያ የምትጠቀምበት ቴክኖሎጂ ለወደፊት አህጉር አቋራጭ ሚሳኤሎችን ለመስራት ሊረዳት ቢችልም፣ በአሁኑ ወቅት ግን አሜሪካን የመምታት ዝግጅቱም ሆነ የቴክኖሎጂ ብቃቱ የላትም ነው የተባለው።
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.