#Ethiopia | በካናዳ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የሮቦቲክስ ውድድር የተሳተፉት የኢትዮ ሮቦቲክስ ታዳጊዎች 3ኛ ደረጃን በማግኘት ለኢትዮጵያ አስደማሚ ድል አስመዝግበዋል።
ይህ ውጤት የኢትዮጵያን ስም በዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂና የሮቦቲክስ መድረክ ከፍ ብሎ እንዲጠራ ያደረገ ሲሆን፣ የታዳጊዎቹን ተሰጥኦ፣ ጥረትና የቴክኖሎጂ ችሎታ ያሳየ ስኬት ሆኗል።
ከውድድሩ አስቀድሞ በ**“ታዲያስ አዲስ”** ፕሮግራም የአውሮፕላን ትኬትና የሆቴል ወጪ ድጋፍ የተደረገለት ተማሪ በዚህ ዓለም አቀፍ ውድድር በመሳተፍ ለውጤቱ አስተዋፅዖ ማድረጉም ተገልጿል።
የዚህ ድል ሌላው ዋና ተዋናይ ኢትዮ ሮቦቲክስ የትምህርትና ውድድር ማዕከል ሲሆን፣ ተቋሙ ባለፉት 15 ዓመታት ታዳጊዎችንና ወጣቶችን በኮዲንግ፣ ዲዛይንና ኢንጂነሪንግ በማሰልጠን ለቴክኖሎጂው ዓለም ሲያዘጋጅ ቆይቷል።
በአዲስ አበባ አራት የሥልጠና ማዕከላትን ከፍቶ እየሰራ ያለው ተቋሙ፣ በቀጣይ ወደ ኮሌጅ ደረጃ ለማደግ በሂደት ላይ መሆኑም ታውቋል።
የዛሬው ድል የነገው የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ተሰጥኦ በዓለም መድረክ ላይ ምን ያህል ሊያበራ እንደሚችል ያሳየ ተስፋ ሰጪ ምልክት ነው።


Source: GetuTemesgen









No comments yet.