693 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ
የጉምሩክ ኮሚሽን ከፌደራልና ከክልል ፖሊስ አባላት ጋር በመሆን ከሀምሌ 23 እስከ ሀምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ባደረገው ክትትል የተያዙት 648 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የገቢ እንዲሁም 44 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የሚገመቱ የወጭ ኮንትሮባንድ እቃዎች ናቸው፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አዳዲስና ልባሽ ጨርቆች፣ የግብርና ምርቶች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒት፣ ማዕድናት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳትና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን ባከናወነው ክትትል ህብረተሰቡ ከፍተኛ ትብብር ማድረጉ የተገለጸ ሲሆን፥ በፍተሻ፣ በጥቆማና በበረራ ከተያዙ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተጨማሪ ሲያዘዋውሩ የተገኙ 30 ተጠርጣሪዎችና 17 ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
ኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን ተጽእኖ ለመከላከል ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.