#Ethiopia | በሰሜን ኮሪያ ፒዮንግያንግ ከ330 ሜትር በላይ ተንደራርቦ የሚገኘውና በ1987 ግንባታው የተጀመረው ባለ 105 ፎቁ የሪዩግዮንግ ሆቴል ከአራት አስርት ዓመታት ገደማ በኋላም አንድም ተስተናጋጅ እንግዳ ሳያገኝ እስካሁን ደረቱን ገልብጦ ይታያል።
ሀገሪቱ የዘመናዊነቷና የታላቅነቷ መገለጫ እንዲሆን አቅዳ የገነባችው ይህ በፒራሚድ ቅርጽ የተሰራ ግዙፍ ሕንፃ በ1990ዎቹ መጀመሪያ በገጠመ ከባድ የኢኮኖሚ ውድቀት ምክንያት ግንባታው ተቋርጦ ለዓመታት በባዶ ኮንክሪትነቱ ቆሞ ነበር።
በሂደት የውጭ መስታወቱ ተገጥሞለት ከፊሉን ክፍሎች ለመክፈት ተደጋጋሚ ዕቅዶች ቢወጡም ሳይሳኩ ቀርተዋል።
የውስጥ አካሉ ሙሉ በሙሉ ባለመጠናቀቁ ምክንያት አሁንም ቢሆን እንደ ሆቴል አገልግሎት መስጠት ያልቻለው ይህ ሕንፃ በአሁኑ ወቅት የውጭ አካሉ መንግሥታዊ መልእክቶችና አኒሜሽኖች የሚያልፉበት ግዙፍ የኤልኢዲ ስክሪን ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.