የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምዝገባ ተጀመረ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጅ እና የአውሮፕላን ጥገና ቦታዎች ምዝገባ ዛሬ ተጀምሯል።

እስከ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም በሚቆየው በዚህ በኦንላይን ምዝገባ አመልካቾች የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን እና መታወቂያቸውን በተለዩ ሁለት የፒዲኤፍ (PDF) ፋይሎች አዘጋጅተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

​የምዝገባ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ በኢንተርኔት የሚከናወን ቢሆንም የጽሁፍ ፈተና እና የኢንተርቪው ሂደቶች በአዲስ አበባ ብቻ የሚሰጡ በመሆናቸው የክፍለ ሀገር አመልካቾች ይህንን ታሳቢ ማድረግ አለባቸው።

የፋይል መጠኑም ከ1 ሜጋባይት መብለጥ የሌለበት ሲሆን ዝርዝር መረጃዎችን እና የአመዘጋገብ ቅደም ተከተሎችን በኩባንያው ይፋዊ ድረ-ገጽ ይከታተሉ።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2