በሰሜን ጎንደር በዝናብ እጥረት በተከሰተ ድርቅ ከ80 ሺህ በላይ ሰዎች ለአደጋ ተጋለጡ፤ 14 ሺህ የቁም እንስሳት ሞቱ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja | በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ ከሚያዝያ አጋማሽ 2018 ዓ.ም ጀምሮ በተከሰተ የዝናብ እጥረት ምክንያት ከ80 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ለከፍተኛ አደጋ መጋለጣቸውንና ከ14 ሺህ በላይ የቁም እንስሳት መሞታቸውን የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

​እንደ ወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ገዛአብ እያሱ ገለጻ ከሆነ፣ በወረዳው ስር በሚገኙ 10 ቀበሌዎች ላይ ምንም ዓይነት ዝናብ ባለመጣሉ ድርቁ በሰውና በእንስሳት ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል። በተጨማሪም በድርቁ ምክንያት ከ9 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ የተዘራ ሰብል ሳይበቅል ቀርቷል።

​በአካባቢው ከድርቁ ጋር ተያይዞ አዳዲስ የጤና ችግሮች እየታዩ ሲሆን፣ የበሽታዎቹን ዓይነትና መንስኤ ለይቶ ለማወቅ የሚያስችል ግብረ-ኃይል ተዋቅሮ የምርመራ ጥናት እየተካሄደ ይገኛል።

​የተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ ከወረዳው አቅም በላይ በመሆኑ አስቸኳይ የምግብ፣ የውሃ እና የእንስሳት መኖ ድጋፍ ያስፈልጋል። በመሆኑም የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት፣ የረድኤት ድርጅቶችና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት በአስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ የወረዳው አስተዳደር ጥሪ አቅርቧል። (ዘገባው የሸገር ሬዲዮ ነው)


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: