በኢትዮጵያ በውርስና ስጦታ ላይ አዲስ ታክስ ሊጣል ነው በኢትዮጵያ በውርስ ወይም በስጦታ በሚገኙ ገቢዎች ላይ አዲስ የታክስ ዓይ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በኢትዮጵያ በውርስና ስጦታ ላይ አዲስ ታክስ ሊጣል ነው
 
በኢትዮጵያ በውርስ ወይም በስጦታ በሚገኙ ገቢዎች ላይ አዲስ የታክስ ዓይነት ሊጣል መሆኑ ተገለጸ።
 
ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የውርስና የስጦታ ገቢዎች ለዚህ ታክስ እንደሚዳረጉ ተመልክቷል።
 
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) የአምስተኛውን ዙር የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም ግምገማ ተከተሎ ይፋ ባደረገው ባለ 132 ገጽ ሙሉ ሪፖርት እንደጠቆመው፣ የአገሪቱ የታክስ መሠረት በጣም ጠባብ በመሆኑ መንግሥት በየዓመቱ የአገር ውስጥ ገቢውን ለማሳደግ አዳዲስ የታክስ ዓይነቶችን ለመተግበር አቅዷል።
 
በዚሁ ሪፖርት መሠረት በውርስና ስጦታ  ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በሚገኝ ገቢ ላይ ታክስ ይጣላል።
 
በሲጋራ፣ በአልኮልና በነዳጅ ምርቶች ላይ የሚጣለው ታክስ እንደሚጨምር የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም አገራዊ ገቢን ከመጨመር ባለፈ ለጤና ፖሊሲዎች አተገባበር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተመልክቷል።
 
የኢኮኖሚ ባለሙያው አቶ ዋሲሁን በላይ በሰጡት አስተያየት፣ እነዚህ አዳዲስ የታክስ እርምጃዎች በአጠቃላይ በአገሪቱ ኢኮኖሚና በህብረተሰቡ ላይ ተጨማሪ ጫና ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።
 
ሆኖም መንግሥት አገራዊ ገቢውን ለማሳደግ ሲል ውሳኔዎቹን በቁርጠኝነት እንደሚተገብራቸው ይጠበቃል ብለዋል።ethio fm
 
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: