በደቡብ አፍሪካ አገልግሎት መስጠት ባቆመ የማዕድን ማውጫ ውስጥ በደረሰ አደጋ በትንሹ የ14 ሰዎች ሕይወት አለፈ። በበርካታ ሰዎ

- Advertisement -
Sidebar AD

በደቡብ አፍሪካ አገልግሎት መስጠት ባቆመ የማዕድን ማውጫ ውስጥ በደረሰ አደጋ በትንሹ የ14 ሰዎች ሕይወት አለፈ። በበርካታ ሰዎች ላይም ጉዳት ደርሷል።

በአደጋው ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች አስክሬን የተገኘው ከጆሃንስበርግ ከተማ በ130 ኪሎሜትሮች ርቀት ላይ በሚገኘው እና በፕላቲንየም ማዕድን በበለጸገችው የሩተንበርግ ከተማ አቅራቢያ መሆኑን የሀገሪቱ ፖሊስ አስታውቋል። የአደጋውን መንስኤ አስመልክቶ ፖሊስ በዝርዝር የሰጠው መረጃ ባይኖርም የግዛቲቱ ፖሊስ አዛዥ ወደ ስፍራው ማቅናታቸውን አሶሽየትድ ፕረስ ዘግቧል።
በሀገሪቱ “ዛማ ዛማስ” በመባል የሚጠሩት ባህላዊ ማዕድን ፈላጊዎች አገልግሎት መስጠት ባቆሙ የወርቅ እና የፕላቲኒየም ማዕድን ማውጫዎች ያለበቂ የደህንነት የደህንነት መሳሪያዎች በህገ ወጥ መንገድ እንደሚሰማሩ ዘገባው አመልክቷል።

እነዚሁ ባህላዊ ማዕድን ፈላጊዎች አብዛኞቹ ከተደራጁ የወንጀል ቡድኖች ጋር ግንኙነት ያላቸው ናቸውም ተብሏል።
በህገ-ወጥ ማዕድን ማውጣት ምክንያት በደቡብ አፍሪካ በቅርብ ጊዜ ከደረሱት ትላልቅ አደጋዎች አንዱ ከሁለት ዓመት በፊት በጎርጎርሳዊው 2024 መገባደጃ ላይ የተከሰተው የበርካታ ሰዎችን ሕይወት ነጥቋል። በወቅቱ በአንድ አገልግሎት መስጠት ባቆመ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ውስጥ መውጫ አጥተው በርካታ ቀናት የወሰደ የሕይወት አድን ጥረት ሲደረግ ቆይቷል።
ወራት የፈጀው የህይወት አድን ጥረት ከአንድ መቶ በላይ ሰዎችን ህይወት ማትረፍ ቢቻልም ከ80 በላይ ሰዎች ግን ለሕልፈት ተዳርገው ነበር ።

በደቡብ አፍሪካ ተመሳሳይ አደጋዎች ተደጋግመው እንደሚከሰቱ የጠቆመው ዘገባው የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ህገ-ወጥ ማዕድን ማውጣትን እና የተደራጁ ወንጀሎችን ለመዋጋት ወታደሮችን በማሰማራት ዘመቻ እያካሄዱ ይገኛሉ ብሏል።

DW Amharic



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1