ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በሐዋርያት ሥራ (11፥29–30) ላይ እንደሚነግረን በሮማው ንጉሥ በቀላውዴዎስ ዘመን በኢየሩሳሌም እና አካባቢዋ ይኖሩ የነበሩ ክርስቲያኖች እጅግ አስከፊ ርሃብ አጋጠማቸው፡፡
ይህ ርኃብ በአንድ ከተማ ወይም በአንድ ቤተሰብ ላይ የደረሰ ችግር ብቻ አልነበረም፤ በርካቶችን ያጠቃ ታላቅ ርኃብ ተብሎ የተገለጸ ሰፊ መከራ ነበር። በዚያን ዘመን የግብርና ኑሮ በዝናብና በአየር ሁኔታ ላይ የተመረኮዘ ስለነበር፣አስከፊው ድርቅ ሲከሰት ለምግብነት የሚውሉ አዝርዕት ጠፉ፤ከባድ ርሃብም ተከሰተ፤በኢየሩሳሌም እና አካባቢዋ ይኖሩ የነበሩ ክርስቲያኖችም በርሃቡ ጽናት የተነሳ ተጨነቁ፡፡
በተለይ በሐዋርያት ሥራ 11፥29–30 እንደምናየው በአንጾኪያ የሚኖሩ ክርስቲያኖች ሁሉም እንደዬ ችሎታው በይሁዳ ለሚኖሩ ወንድሞች እርዳታ እንዲላክ አድርገዋል፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም የአንጾኪያ ክርስቲያኖች በይሁዳ የነበሩትን የተራቡ ወንድሞች ለመርዳት መነሳታቸውን እንደ ታላቅ የፍቅርና የአንድነት ምሳሌ አድርጎ ያቀርባል። ይህም ርኃብ በሰው ላይ የሚያመጣውን ሥቃይ አይቶ ዝም ብሎ ማለፍ ሳይሆን፣ ያለንን ከተራበው ጋር መካፈል የክርስቲያናዊ ፍቅር መገለጫ መሆኑን ያስተምረናል።
ዛሬም በዚህ በኛ ዘመን ለስጋችን የበረከት ማግኛ ለነፍሳችንም ስንቅ እንድንይዝ የበረከት ስራን እንድንሰራ ጥሪ ቀርቦልናል፡፡“ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም” በከባድ ንፋስና ዝናብ ምክንያት ቤተ መቅደሱ ፈርሶ ይገኛል፣ መነኮሳቱም በድርቅና በርሃብ ከባድ ፈተና ውስጥ ሆነው ድጋፋችንን እየጠበቁ ነውና የድጋፍ እጃችንን እንዘርጋላቸው።
በረሃብ ውስጥ መኖር የዕለት እንጀራን ብቻ ማጣት ሳይሆን ጤናን፣ ክብርንና ተስፋን የሚፈታተን አስከፊ ሕይወት ነውና ካለን ላይ በማካፈል ገዳማዊያኑን እንርዳ፣ለነፍሳችንም ስንቅን እንያዝ።
ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡- 1000766349227
አቢሲንያ ባንክ ፡- 262281132
ለበለጠ መረጃ:- 0944672222 ወይም 0916106921
Source: FastMereja









No comments yet.