ጥንዶቹ 23,000 ኪሎ ሜትሮችን ተጉዘው ከ222 ቀናት በኋላ ናይሮቢ ደረሱ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | እንግሊዛውያኑ ጥንዶች ከለንደን እስከ ናይሮቢ ያደረጉትን የ23 ሺህ ኪሎ ሜትር የመኪና ጉዞ አጠናቀቁ።

ሁለቱ እንግሊዛውያን ኤምና ሳም “ዘ አድቬንቸር ዌይ” (The Adventure Way) በሚል መጠሪያቸው ከለንደን ተነስተው እስከ ናይሮቢ በየብስ ያደረጉትን የ23,000 ኪሎ ሜትር ጉዞ በ222 ቀናት ውስጥ በስኬት አጠናቀው ኬንያ ገብተዋል።

ጥንዶቹ ጉዟቸውን ከአውሮፓ በመነሳት በርካታ የአፍሪካ አገራትን አቋርጠው ወደ ምስራቅ አፍሪካ መድረስ ችለዋል።

በጉዟቸው ወቅት የአፍሪካን አስቸጋሪ የመሬት አቀማመጥና ፈታኝ መንገዶችን ያለፉ ሲሆን ይህም ጉዞአቸው አህጉሪቱን በቅርበት እንዲረዱና አስደናቂ ተሞክሮ እንዲያገኙ ረድቷቸዋል።

ጥንዶቹ ናይሮቢ መድረሳቸው አድርገው አውሮፓንና አፍሪካን በየብስ ያገናኘው አስደናቂ የመንገድ ላይ ጉዞአቸው ከብዙዎች አድናቆት እንዲቸራቸው አድርጓል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#England #couples
#London #Nairobi
#travel #Africa
#overland


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2