ታዋቂው ዲጄ ሚካኤል ቫንዴዌርት በ28 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ያለ ጊዜው እርጅናን በሚያስከትለው የፕሮጄሪያ ሕመም ሲታገል የቆየውና በማህበራዊ ሚዲያ አዎንታዊ የሕይወት አመለካከቱን በማሰራጨት የሚታወቀው የ28 ዓመቱ ቤልጂየማዊ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሚካኤል ቫንዴዌርት በልብ ሕመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

የሕክምና ባለሙያዎች ከ12 ዓመት በላይ አይኖርም ብለው ገምተው የነበረ ቢሆንም በእግዚአብሔር ፍቃድ ፤ ባሳየው ጠንካራ የመኖር ፍላጎትና ተስፋ ያለመቁረጥ መንፈስ በበሽታው ከተጠቁ ሰዎች መካከል ረጅም ዕድሜ ከኖሩት ጥቂቶች አንዱ እንዲሆን አድርጎታል።

​በዲጄነትና በቪዲዮ ጌም ይዘት አዘጋጅነቱ ወደ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ተከታዮችን ያፈራው ሚካኤል “ሕይወት አጭር ናት፣ በአግባቡ ተጠቀምባት” በሚለው ትምህርታዊ መልእክቱና ባሳተማቸው ሥራዎቹ በርካታ ሰዎችን ሲያነሳሳ ቆይቷል።

ከእርሱ ጋር ተመሳሳይ ሕመም ካለባት የ20 ዓመት እህቱ አምበር ጋር በመሆን የተስፋ ምልክት ሆኖ የዘለቀው የዚህ ወጣት ማለፍ በርካቶችን ያሳዘነ ሲሆን ታዋቂው ግብ ጠባቂ ቲቦ ኮርቱዋ እና የኬአርሲ ጄንክ እግር ኳስ ክለብን ጨምሮ በርካቶች ለቤተሰቡና ለወዳጆቹ መጽናናትን ተመኝተዋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2