የምክክር ኮሚሽኑ የተመሰረተበት ዋና አላማ የሆነው አጀንዳ ፀደቀኢትዮጵያ በፕሬዚዳንት እንድትመራ ተመካካሪዎች ሙሉ በሙሉ መግባባ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የምክክር ኮሚሽኑ የተመሰረተበት ዋና አላማ የሆነው አጀንዳ ፀደቀ🙄🙄
ኢትዮጵያ በፕሬዚዳንት እንድትመራ ተመካካሪዎች ሙሉ በሙሉ መግባባት መደረሳቸው ታውቋል።
ኢትዮጵያ በጠ/ሚኒስትር ቀርቶ በፕሬዚዳንት እንድትመራ፣ የመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ፣ እንዲሁም የፖለቲካ ሥርዓት፣ የፖለቲካ ውክልናና የምርጫ ሥርዓት አጀንዳ ላይ የ500 ቡድን ተመካካሪዎች ሙሉ በሙሉ ተሰምቷል።
በዚሁ አጀንዳ ላይ ተወያይ የነበሩ ተመካካሪዎች ለሪፖርተር በሰጡት አስተያየት፣ በቀረቡት አብዛኞቹ ምክረሐሳቦች መግባባት ላይ መደረሱን ሆኖም ያላግባቡና ወደ ቀጣይ የተሻገሩ ጉዳዮች መኖራቸውንም ገልጸዋል።
በዚህም የ500 ቡድን ተመካካሪዎች የአገሪቱ አስተዳደር ሥርዓት ፓርላሜንታሪ ሆኖ እንዲቀጥል፣ የአገሪቱ መሪ ፕሬዚዳንት እንዲሆን፣ አዲሱ ተመራጭ ፕሬዚዳንትም የጠቅላይ ሚኒስትሩና የፕሬዚዳንቱ ሥልጣንና ተግባርን ጠቅልሎ እንዲወጣ በምክረሐሳብ ደረጃ ከመግባባት ላይ መደረሱን፣ ይህም ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲቀር የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል።
የአገሪቱ መሪ የሥልጣን ዘመን 6 ዓመት ሆኖ ለሁለት ዙር እንዲደረግ፣ የክልል መሪዎችም ከፌዴራሉ ጋር ተመሳሳይ እንዲሆን በምክረሐሳብ ደረጃ ከመግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል።
የሕገመንግሥት ጉዳዮች ተርጓሚ ፍርድ ቤት እንዲቋቋም፣ አሁን ያለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አሠራር ያልመለሳቸው የማንነትና የራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄዎች “ሕብረ ብሔራዊ አንድነት ኮሚሽን” የሚል ሥያሜ ያለው ገለልተኛ ተቋም በአስቸኳይ ተቋቁሞ በአጭር ጊዜ ውስጥ ምላሽ እንዲሰጥባቸው ለዚህም ይረዳ ዘንድ ልዩ የባለሙያዎች ቡድን እንዲቋቋም በምክረሐሳብ ደረጃ ከመግባባት ላይ ተደርሷል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1