#Ethiopia | በቻይና ሻንጋይ በተካሄደው “ሶሊሞ ሶርሲንግ ሻንጋይ ኩዌይ” የዓለም አቀፍ የቡና ጨረታ ላይ የኢትዮጵያ ልዩ ቡና አዲስ የዓለም የዋጋ ሪኮርድ በማስመዝገብ በታሪክ ያልታየ ከፍተኛ ዋጋ አገኘ።
በዚህ ታላቅ ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ አንድ ኪሎግራም የኢትዮጵያ ቡና በ2,275 የአሜሪካ ዶላር (ከ364 ሺህ የኢትዮጵያ ብር በላይ) በመሸጥ የኢትዮጵያ የቡና ክብርን ከላይ ሰቅሎታል።
እንደ ስፑትኒክ ዘገባ ይህ ታሪካዊ ዋጋ ያወጣው ቡና በሲዳማ ክልል በንሳ በተባለው አካባቢ በአርሶ አደሮች በጥንቃቄ የተመረተ ሲሆን በዘመናዊው “አናኢሮቢክ” የማቀናበሪያ ዘዴ ተዘጋጅቶ ለገበያ የቀረበ ነው።
ቡናው ያለው ተፈጥሯዊ ጣዕም፣ ልዩ መዓዛና ከፍተኛ የጥራት ደረጃ በጨረታው ላይ በተገኙ የዓለም አቀፍ ቡና ገዢዎች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን ያተረፈ ሲሆን የሀገራችንን ቡና አምራቾች የላቀ ጥረትና የኢትዮጵያን የቡና ገበያ ገናናነት በዓለም አቀፍ ደረጃ በድጋሚ ያረጋገጠ ትልቅ ነው።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.