#Ethiopia | ፑቲን አወዛጋቢዎቹን የኩሪል ደሴቶች መጎብኘታቸው ከጃፓን ተቃውሞ ገጥሟቸዋል።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሩሲያና በጃፓን መካከል ታሪካዊ የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸውን በፓሲፊክ ውቅያኖስ የሚገኙትን የኩሪል ደሴቶችን ጎብኝተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ደሴቶቹን መጎብኘታቸው በቶኪዮ በኩል ከፍተኛ ተቃውሞ አስከትሎባቸዋል።
የጃፓኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳናኤ ታካኢቺ የፑቲን ጉብኝት በፍፁም ተቀባይነት የሌለው እና የጃፓንን ህዝብ ስሜት የጎዳ ነው ሲሉ ኮንነዋል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን በስልጣን ዘመናቸው ደሴቶቹን ሲጎበኙ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
የጃፓን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሩሲያ አምባሳደርን በመጥራት ይፋዊ የተቃውሞ ደብዳቤ መስጠታቸው አልጀዚራ ዘግቧል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ታካኢቺ ደሴቶቹ በታሪክም ሆነ በዓለም አቀፍ ሕግ የጃፓን አካል መሆናቸውን ገልጸው ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ እንደሚያበላሸው አስረድተዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#Russia #kuril #islands
#Japan #primeminister
Source: GetuTemesgen








No comments yet.