ሌስተርን ሲቲን መግዛት የሚፈልግ ወደ ኪንግ ፓወር ጎራ ይበል ተብሏል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የእንግሊዙ ሌስተር ሲቲ እግር ኳስ ክለብ ባለቤቶች የሆኑት ታይላንዳዊው ኪንግ ፓወር ኩባንያ ከ16 ዓመታት የባለቤትነት ቆይታ በኋላ ክለቡን ከ200 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ በሆነ ዋጋ ለመሸጥ ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸው ተገለጸ።

የሲቲ ግሩፕ የኢንቨስትመንት ባንክ ክለቡን የሴቶች ቡድኑን የ32 ሺህ ተመልካች የመያዝ አቅም ያለውን ኪንግ ፓወር ስታዲየም በ121 ሚሊዮን ፓውንድ የተገነባውን ዘመናዊ የስልጠና ማዕከል እንዲሁም ኦኤች ሊቨን የተሰኘውን የቤልጂየም እህት ክለብ በአንድ ላይ አጠቃሎ የያዘ ‘ፕሮጀክት ላይንአፕ’ የተሰኘ ስምንት ገጽ ያለው የሽያጭ ማስተዋወቂያ ሰነድ አዘጋጅቶ ለገዢዎች ማቅረቡ ታውቋል።

​የቀድሞው የፕሪሚየር ሊግ እና የኤፍ ኤ ካፕ አሸናፊ የሆነው ሌስተር ሲቲ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ተከታታይ ውድቀቶች አስተናግዶ ወደ ሶስተኛው የውድድር እርከን (ሊግ ዋን) የወረደ ቢሆንም የሽያጭ ሰነዱ የክለቡን ታሪካዊ ስኬቶች እና አዋጭነት በጎላ ሁኔታ አጉልቶ አቅርቧል።

በአንፃሩ ክለቡ በቅርብ ዓመታት ያጋጠመውን የ180 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ከባድ የፋይናንስ ክሳራ እና ያለበትን የ103.6 ሚሊዮን ፓውንድ የባንክ ዕዳ በሰነዱ ላይ ሳይጠቀስ አልፏል።

በ2010 እ.ኤ.አ ክለቡን በ35 ሚሊዮን ፓውንድ የገዙት የሲቫድናፕራባ ቤተሰቦች ክለቡን ለረጅም ዓመታት ሲመሩ የቆዩ ቢሆንም የክለቡ ውጤት ማሽቆልቆል እና በታይላንድ የሚገኘው የኪንግ ፓወር የንግድ እንቅስቃሴ መዳከም ባለቤቶቹ ክለቡን እንዲሸጡ ምክንያት ሆኗል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: