የፊደል ካስትሮ 100ኛ ዓመት የመታሰቢያ በዓል ተከበረ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia |ኩባ የፊደል ካስትሮን 100ኛ አመት የልደት መታሰብያ ያከበረችው በአሜሪካ ከባድ የኢኮኖሚ እና የነዳጅ ማዕቀብ ውስጥ ሆና ነው።

የፊደል ካስትሮ የ100ኛ ዓመት የልደት መታሰቢያ መርሃ ግብር የተካሄደው የትራምፕ አስተዳደር ባለፈው የፈረንጆቹ ጥር ወር የነዳጅ እገዳ ከጣለ ወዲህ በሀገሪቱ ላይ የተደቀነው የኢኮኖሚ ጫና በተጠናከረበት ወቅት ነው።

አሜሪካ በኮሙኒስቷ ሀገር መንግሥት ላይ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎችን ለማስገደድ ያለሙ ተከታታይ ማዕቀቦችን ጥላለች።

እነዚህ እርምጃዎች ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የነበረውን የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ቀውስ የበለጠ እንዲባባስ አድርገዋል።

የአሜሪካ ማዕቀብ እና በሀገር ውስጥ የተደረገው የፖሊሲ ማሻሻያ ተጎድቶ የቆየውን የኩባ ኢኮኖሚ የበለጠ ቀውስ ወስጥ አስገብቶታል ተብሏል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#ChinaBulletTrain
#Cuba #FidelCastro
#Birthday #USA #Sanction
#Economy #policy


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: