አሜሪካ በኬንያ ላይ ከባድ ማዕቀብና
ታሪፍ ልትጥል ትችላለች ተባለ
አሜሪካ፣ ኬንያ በአጎዋ (AGOA) የቀረጥ ነጻ ዕድል ሽፋን የቻይና ምርቶችን መልሳ በማሸግ ወደ አሜሪካ ሳትልክ አትቀርም የሚል ጥርጣሬ እንዳላት በይፋ ገለጸች። ሰሞኑን የወጣ አንድ የአሜሪካ መንግሥት ሪፖርት እንዳመለከተው፣ የቻይና ኩባንያዎች የኬንያን ርካሽ ጉልበትና የወደብ አገልግሎት ለመጠቀም ሲሉ ምርታቸውን ወደ አገሪቱ ሳያዛውሩ አልቀሩም። ኬንያ በዚህ ድርጊት መሳተፏ ከተረጋገጠ፣ ከባድ ማዕቀብና ታሪፍ ሊጣልባት ወይም ከአጎዋ የቀረጥ ነጻ ዕድል ልትታገድ እንደምትችል አሜሪካ አስጠንቅቃለች።
በሌላ በኩል፣ የአሜሪካ መንግሥት በቻይና ግብዓቶች ኢትዮጵያ ውስጥ የተመረቱ ሶላር ፓነሎች በቻይና ምርቶች ላይ የተጣሉ ታሪፎችን በመተላለፍ ወደ አሜሪካ ይላካሉ በሚለው ውንጀላ ላይ ምርመራ ሊጀምር መኾኑን በቅርቡ መግለጡ ይታወሳል።
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.