በኢንግሊዝ ሃገር በቤተክርስቲያን ደጅ አዛውንት የደፈረው ኤርትራዊ ስደተኛ ጥፋተኛ ተባለ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በሰሜን ለንደን በሚገኝ ቤተክርስቲያን ደጅ አንዲት አዛውንት በመድፈር ወንጀል የተከሰሰው ብሩክ ደሳለኝ የተባለው የ33 ዓመት ኤርትራዊ በሃሮው ክራውን ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተባለ።

የዳኞች ቡድኑ የክትትል ካሜራ (CCTV) ምስሎችንና የዓይን እማኞችን ማስረጃ ከተመለከተ በኋላ ተከሳሹ ጥፋተኛ መሆኑን አረጋግጧል።

​ተከሳሹ ጥቃቱን የፈጸመው በሃሮው ሴንት ጆን ቤተክርስቲያን አቅራቢያ አግዳሚ ወንበር ላይ ተቀምጠው የነበሩትንና በከፍተኛ ሁኔታ ሰክረው የነበሩትን አዛውንት ሰው ወደ ሳር ላይ በመጎተትና ከማስታወቂያ ሰሌዳ ጀርባ በመሸሸግ እንደነበር ተገልጿል።

ለ20 ደቂቃዎች ያህል ጥቃቱን ሲፈጽም በአካባቢው ያለች አንዲት የዓይን እማኝ ምስክር ሁኔታውን በመስኮቷ በኩል ተመልከታ በስልኳ በመቅረፅ ለፖሊስ ጥቆማ መስጠቷን ተከትሎ የለንደን ሜትሮፖሊታን ፖሊስ በ5 ደቂቃ ውስጥ ቦታው በመድረስ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር አውሎታል።

​ተከሳሹ መጀመሪያ ላይ “አዛውንቱን ልረዳቸው ነው” የሚል ምክንያት ቢያቀርብም የካሜራ ምስሉ ካሳዩት በኋላ ግን ዝምታን መርጧል።

ፍርድ ቤት የቅጣት ውሳኔውን ለመስጠት ቀጠሮ ይዟል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: