#FastMereja I ከረጅም የጉዳት እና የህክምና ጊዜ በኋላ ወደ እግር ኳስ የተመለሰው አጥቂው አቡበከር ናስር፣ ከቀድሞ ክለቡ ኢትዮጵያ ቡና በኩል ምንም አይነት ጥያቄ ስላላቀረበለት ቀጣይ ማረፊያው መቻል ስፖርት ክለብ መሆኑን አስታውቋል።
ተጫዋቹ ይፋ ባደረገው መግለጫ፣ ከጉዳቱ በመልቀቅ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲመለስ ቀዳሚ ምርጫው ኢትዮጵያ ቡና እንደነበር ገልጿል። ቀደም ሲል ለደቡብ አፍሪካው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ሲፈርም የኢትዮጵያ ቡና አመራሮችና ደጋፊዎች ያደረጉለትን ድጋፍ ያወሳው አቡበከር፣ ወደ ሀገር ውስጥ ለመመለስ ፍላጎቱን በይፋ ቢገልጽም ከቡና በኩል ያናገረው አካል አለመኖሩን አስረድቷል።
በዚህም ምክንያት ከሌሎች ክለቦች የመጡለትን ጥያቄዎች ሲጠባበቅ የቆየ ቢሆንም፣ ከኢትዮጵያ ቡና ምላሽ በማጣቱ የመቻል ስፖርት ክለብን ጥያቄ በመቀበል ለመፈረም መወሰኑን አረጋግጧል። አቡበከር ለአዲሱ ክለቡ መቻል ስፖርት ክለብ ምስጋናውን አቅርቦ፣ የክለቡን ግቦች ለማሳካት ቁርጠኛ መሆኑን ሲገልጽ፤ ለኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎችም ያለውን ፍቅርና አክብሮት አግልጿል።
Source: FastMereja








No comments yet.