ጓደኛችን በጭራሽ ብቻሽን አይደለሽም!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ተማሪዎቹ በካንሰር ለታመመችው የትምህርት ቤት ጓደኛቸው የጓደኝነት እና የርኅራኄ ጥግ የታየበት ተግባር ፈፅመዋል።

ተማሪዎቹ የጓጀኛቸውን ሕመም መጋራት ባይችሉም ብቸኝነቷን ማስረሳት ችለዋል።

በሕይወት መንገድ ላይ የሚያጋጥሙ ፈተናዎች አንዳንዴ እጅግ ከበድ ያሉ እና ብቸኝነት የሚሰማቸው ናቸው።

በተለይም በካንሰር ሕክምና ምክንያት የሚከሰት የፀጉር መርገፍ አእምሮአዊ እና ስሜታዊ ፈተናው በቀላሉ የሚገለጽ አይደለም።

በዚህች ተማሪ የደረሰውም ልክ እንደዚሁ ተመሳሳይ ታሪክ ነበር።

ነገር ግን ተማሪዋ ይህ አስቸጋሪ እና አስፈሪ ምዕራፍ በጓደኞቿ ዘንድ ልዩ የፍቅር ማሳያ ሆኖ አልፏል።

የጓደኛቸውን ህመም እና ስቃይ በቀጥታ ማስወገድ እንደማይችሉ የተረዱት የትምህርት ቤቷ ተማሪዎች እሷን የሚያረጋጋ እና ትልቅ ብርታት የሚሰጣት አስደናቂ ተግባር ፈጸሙ።

በካንሰር ምክንያት ፀጉሯ የረገፈውን ጓደኛቸውን ለመምሰል 70 የሚጠጉ የትምህርት ቤቱ ወንድ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ፀጉራቸውን በመላጨት ጓደኛቸውን መስለዋል።

አንዳንዴ የሰዎችን ሕመም ሙሉ በሙሉ ማቅለል ባንችል እንኳ በፈተናቸው ጊዜ አብረናቸው በመቆም ብቸኝነት እንዳይሰማቸው ማድረግ ትልቅ ፈውስ እንደሆነ ይህ አጋጣሚ ያስመሰክራል።

ይህ የተማሪዎቹ ድርጊት ተራ የፀጉር መላጨት ሳይሆን የጓደኝነት ፍቅር የርኅራኄ፣ የደግነት እና ጥልቅ የሆነ የሰው ልጅ ስሜታዊ ትስስር ማሳያ ነው።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#cancer #treatment
#Schools #students
#friendship #compassion #solidarity


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: