በአሜሪካ የሚኖሩ ከ5 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ሃገሪቷን ለቀው እንዲወጡ ታዘዙ
በአሜሪካ የፌዴራል ፍርድ ቤት የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከ5 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ተሰጥቶ የነበረውን ጊዜያዊ የህጋዊ መኖሪያ እና የስራ ፈቃድ ጥበቃ (TPS – Temporary Protected Status) እንዲያበቃ ውሳኔ አስተላለፈ።
የፌዴራል ዳኛ ብሪያን ሙርፊ ማክሰኞ ዕለት ባስተላለፉት ውሳኔ፣ የሃገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት (DHS) በኢትዮጵያውያን ላይ የነበረውን የTPS ጥበቃ ለማቋረጥ ያቀደውን እርምጃ እንዳይፈጽም ታግዶ የቆየውን የህግ እገዳ በማንሳት የትራምፕ አስተዳደር እርምጃውን እንዲቀጥል ፈቅደዋል።
📌 ከውሳኔው ጀርባ የተካሄዱ ዋና ዋና ነጥቦች
ጊዜያዊ የህጋዊ መኖሪያ ጥበቃ (TPS) በኢትዮጵያ በነበረው የፖለቲካና የፀጥታ ችግር ምክንያት በጆ ባይደን አስተዳደር ወቅት በ2022 ተሰጥቶ የነበረ ነው።
የፌዴራል ዳኛው ይህንን እገዳ ያነሱት፣ የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት (Supreme Court) ባለፈው ሰኔ ወር የትራምፕ አስተዳደር የTPS ጥበቃዎችን የማቋረጥ ስልጣን እንዳለው የሰጠውን ውሳኔ ተከትሎ ነው።
ምንም እንኳን ህጋዊ የመኖሪያ እና የሰራ ፈቃዱ የመሰረዝ ሂደት የሚቀጥል ቢሆንም፣ የውሳኔውን ህገ-መንግስታዊነት አስመልከቶ የተመሰረተው ክስ በፍርድ ቤት ውይይት እንደሚደረግበት ተገልጿል።
ውሳኔውን ተከትሎ በአሜሪካ የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንና ቤተሰቦቻቸው አዲስ የህግና የመኖሪያ ስጋት ውስጥ ወድቀዋል።
@Seledadotio

No comments yet.