በሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዜጎች መካከል እየተፈጸመ ያለውን ጥቃት በተመለከተ ይፋዊ መግለጫ አወጣ::በሳዑዲ …

- Advertisement -
Sidebar AD
በሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዜጎች መካከል እየተፈጸመ ያለውን ጥቃት በተመለከተ ይፋዊ መግለጫ አወጣ::
በሳዑዲ አረቢያ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲ (ሪያድ) ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ኢትዮጵያውያን እርስ በርሳቸው ሲደባደቡና ጥቃት ሲፈጽሙ የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን በተመለከተ ጉዳዩን በትኩረት እየተከታተለው መሆኑን እና አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመሆን የምርመራ ስራ መጀመሩን አስታወቀ።
* በዚህ ኢሰብአዊ ተግባር ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች መደበኛ ባልሆነ (በህገ-ወጥ) መንገድ ወደ ሳዑዲ አረቢያ የገቡ ናቸው። እነዚህ አካላት በበረሃና ገጠራማ አካባቢዎች በመሸሸግ፣ ምክንያታቸው በግልጽ ባልታወቀ ጉዳይ ቡድን (ጎራ) በመፍጠር እርስ በርሳቸው ግጭት ሲፈጥሩ እንደነበር ተደርሶበታል።
* እስካሁን በተደረገው ክትትልና ጥረት አንድ ተጠራጣሪ በሳዑዲ አረቢያ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።
ኤምባሲው ችግሩን ከምንጩ ለማድረቅና በዚህ ወንጀል የተሳተፉትን ሁሉ ለህግ ለማቅረብ ከሚመለከታቸው አካላትና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በቅርበት እየሰራ ይገኛል።
ኤምባሲው እነዚህን ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚያስችል ማንኛውንም ተዛማጅ መረጃ ወይም ጥቆማ ያለው ወገን በአስቸኳይ ለኤምባሲው እንዲያቀርብ በአክብሮት ጥሪ አስተላልፏል።
Via፦ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲ – ሪያድ
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1