በታዩ ደንደአ ላይ የተሰጠው ፍርድ ጸና

- Advertisement -
Sidebar AD

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ደ ኤታ አቶ ታዬ ደንደዓ ላይ በስር ፍርድ ቤት የተሰጠውን የአራት ዓመታት እስር ፍርድ አጸና። ትናንት ረቡዕ ነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. አዲስ አበባ ውስጥ ያስቻለው ፍርድ አቶ ታዬ ያቀረቡትን ይግባኝ ውድቅ በማድረግ ነው ውሳኔውን ያስተላለፈው። አቶ ታዬ ከዚህ በፊት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በቀረበባቸው «ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት» በሚለው ክስ የሰባት ዓመት እስር ከተወሰነባቸው በኋላ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤት ብለው ቅጣቱ ወደ አራት ዓመት እስር ተሻሽሎሏል።

ባለቤታቸው ወ/ሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ ለዶቼ ቬለ እንደተናገሩት በዚህም ላይ ቅሬታ የነበራቸው አቶ ታዬ አምስት ነጥቦችን ዘርዝረው ለፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት አቤት ቢሉም የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ትናንት በዋለው ችሎት ብይኑ ጸንቶባቸዋል። አቶ ታዬ የጦር መሳሪያ ይዘው መገኘታቸውን ከዚህ በፊትም በነበረው የክስ ሂደት አላስተባበሉም ያሉት ባለቤታቸው፤ ከሌላው ዜጋ እኩል የመዳኘት መብት ስለመነፈጋቸውና ካቀረቡት አምስት ተከላካይ ምስክሮች የሁለቱ ቃል ብቻ ተሰምቶ በከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰጠቱንም በቅሬታ ማቅረባቸውን ገልጸዋል።

አቶ ታዬ ትናንት ውሳኔው ከጸናባቸው የክስ ጭብጥ በተጨማሪ አቃቤ ሕግ ይግባኝ በጠየቀበት ሌላው ተጓዳኝ የክስ ጭብጥ ላይ ለጥቅምት 17 2019 ዓ.ም. መቀጠራቸውን ሥዩም ጌቱ ከአዲስ አበባ የላከው ዜና ያስረዳል።

DW Amharic



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2