በዛሬው ዕለት ተመካካሪዎች የተስማሙባቸውን ምክረ ሃሳቦች ለ4 ሺህ ጉባኤተኞች አቅርበው ያጸድቃሉ ተብሎ ቢጠበቅም፣ የኦሮሚያ ክል

- Advertisement -
Sidebar AD

በዛሬው ዕለት ተመካካሪዎች የተስማሙባቸውን ምክረ ሃሳቦች ለ4 ሺህ ጉባኤተኞች አቅርበው ያጸድቃሉ ተብሎ ቢጠበቅም፣ የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች አዲስ አበባን በሚመለከተው ምክረ ሃሳብ ላይ ቅሬታ በማቀረባቸው ምክረ ሃሳቦቹ ሳይጸድቁ ቀርተዋል።

የአዲስ አበባ ባለቤትነት ጉዳይን በተመለከተ በትናንትናው ዕለት በዓምስት መቶ (500) ደረጃ በተነበበው ሰነድ ላይ በሰፈረው መሠረት ይፈረማል ተብሎ ቢጠበቅም፣ የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች በሕገ መንግሥቱ ላይ አዲስ አበባ ዋና መቀመጫ መሆኗ ይደንግግ የሚል ቅሬታ ለኮሚሽኑ በማቅረባቸው ምክረ ሃሳቡ ዳግም እንዲታይ ምክንያት መሆኑን ተሳታፊዎች ነግረውናል።

ጉዳዩ ዳግም መታየት የለበትም፤ በ500 ቡድን ደረጃ ተስማምተናል ያሉ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ለኮሚሽኑ ቅሬታ ማቅረባቸውን አስረድተዋል።

በትናንትናው ዕለት ማለትም ነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ለርዕሰ ቡድን ተመካካሪዎች በንባብ የቀረበው ሰነድ ግን “አዲስ አበባ የፌደራል ከተማ ትሁን፤ ራሷን በራሷ ታስተዳድር” በሚለው ላይ ሁሉም ከስምምነት መድረሱን ያስረዳል፤ ክልሉ ከከተማው አስተዳደር ልዩ ጥቅም ማግኘት ስላለበት የሚደንግገው የሕገ መንግሥቱ ክፍልም “የጋራ ጥቅም” በሚል እንዲሻሻል ከስምምነት መደረሱን ያክላል።

አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል ዋና መቀመጫ ትሁን ከሚለው ጋር በተያያዘ ግን ሁለት ምክረ ሃሳቦች ቀርበው ነበር። እነሱም፦ ክልሎች የራሳቸውን መቀመጫ መወሰን እንዲችሉ በሕገ መንግሥቱ ይካተት የሚለው አንደኛው ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 47 (ወይም አግባብ ያለው አንቀጽ) ላይ የሰፈረው አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል መቀመጫ ከመሆኗ ጋር በተያያዘ ከተማዋን እና ክልሉን የሚመለከቱ ጉዳዮች በሕግ ይወሰኑ የሚል ድንጋጌ ይካተት የሚሉት ናቸው።

ይሁንና የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች “አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል ዋና ከተማ መሆኗ በሕገ መንግሥቱ መካተት አለበት” የሚል ቅሬታ ለ500 ቡድን ከተነበበ በኋላ ዳግም በማንሳታቸው፣ ዛሬ ምክረ ሃሳቦችን ያጸድቃል ተብሎ የነበረው ጉባኤተኛ በምክክር ስፍራው ውሎ ተመልሷል።

በዚህም ምክንያት ጉዳዩን ዳግም የሚመለከት ኮሚቴ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ተወካዮች ተመርጧል።

ኮሚሽኑ ጉዳዩን አስመልክቶ የቀረበለትን ቅሬታ ለመመልከት የክልል ምክር ቤት ጉባኤ ጠርቶ ምክረ ሃሳቡን ከ10 ወይም ገና ከጀመሩት የተሰጡ የቡድን ምክረ ሃሳቦችን ዳግም እንዲመለከቱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከክልል፣ ከሁለቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች፣ ከሽማግሌዎች እና ከሌሎች ቡድኖች ተወካዮች ተመርጠው እስከ ዛሬ ማታ ድረስ ጉዳዩን እንዲያጠናቅቁ ከኮሚሽኑ እንደተነገራቸው ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የክልል ጉባኤ አባል ነግረውናል።

በሌላ በኩል የሂደቱን ወደ ኋላ መመለስ የተቹ እና ለኮሚሽኑ ቅሬታ ያቀረቡ ወገኖች መኖራቸውን ሰምተናል፤ ተመካካሪዎቹ “በትናንትናው ዕለት በ500 ቡድን ደረጃ በንባብ በቀረበልን ምክረ ሃሳብ ላይ ተስማምተን ሳለ እንደገና ወደ ጉዳዩ አድሮ እንደ አዲስ መታየቱ አግባብ አይደለም፤ የኮሚሽኑ የአሰራር ስርዓትም አይፈቅድም” ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል።

እስካሁን ባለው ሂደት ከአዲስ አበባ አጀንዳ ውጪ በሁሉም ምክረ ሃሳቦች ላይ ከስምምነት መደረሱን ከተመካካሪዎች ሰምተናል።

የምክክር ኮሚሽን ምክረ ሀሳቦች በተመካካሪዎች ይጸድቃሉ ብሎ የነበረው ነሃሴ 12 ቀን ነበር።

ይሁናን በትናንትናው እለት በሰጠው መግለጫ ደግሞ ዛሬ ነሃሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ነው።

ይሁንና በሁለቱም ቀን በተበላይ ቀነ ገደብ ምክረ ሀሳቦች 4ሺ ጉባዔተኛ አልቀረበም።

ያሬድ እንዳሻው




Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1