“አ-ሱ-ሪ-ቴ “የአዲስ አመት መምጣት ብስራት-ቃለአብ ከሃሊ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የአዊ ብሄ/አስ ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ስለዘንድሮው አ-ሱ-ሪ-ቴ በዓል አከባበር ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጧል።

‎አሮጌው ዓመት መሸኘቱን – አዲሱ ዓመት መምጣቱን የሚያበስር በየዓመቱ ህፃናት፣ ልጃገረዶችና ታዳጊዎች በጉጉት የሚጠበቅ ውብ ባህላዊ ገጽታ በአገው ምድር ፥አሱሪቴ

‎ነጭ የለበሱ የአገው ምድር ልጃገረዶች እና ታዳጊዎች ድንቅ ዝማሬ እያዜሙ የሚታደሙበት የአሱሪቴ በዓል እየደረሰ ነው።

‎የአዲስ ዓመት መምጣት ብስራት ከሆኑ የድንቅ ምድር ድንቅ ክብረ በዓላት አንዱ የሆነው” የአሱሪቴ” በዓል በልጃገረዶችና ታዳጊዎች ዘንድ በናፍቆት የሚጠበቅ የፍቅር፣ የደስታ፣ የህብረትና የበረከት መግለጫዎች ናቸው።

ለጨዋታው የሚወጡ ልጃገረዶች ነጭ ለብሰው በእጃቸው አረንጓዴ ቄጤማ በመያዝ የክረምቱን ማለፍ እና የአዲስ ዘመን መምጣትን ያበስራሉ።

‎ልጃገረዶች ነጭ ለብሰው የውኃውን መጉደል፣ የክረምቱ ጨለማ ማለፍን እና የጋራ ሸንተረሩ መለምለምና ማበብን በአደይ አበባ አስጊጠው ወደ ጎረቤትና ዘመድ አዝማድ ቤት በመሄድ ይጨፍራሉ፦

የአዊ ብሄ/አስ ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ሀላፊ ቃለአብ ካሃሊ ፥አሱሪቴ” የአዲስ ዘመን መሸጋገሪያ በዓል መሆኑን ገልጸዋል ።

የአገው ማህበረሰብ ኑሮው የተመሰረተው በእርሻ ስራ ላይ መሆኑን የጠቆሙት ሀላፊው በአብዛኛው ሕጻናት፣ ወጣቶች እና ልጃገረዶች የሚሳተፉባቸው እና የመጫዎቻ፣ የመደሰቻ፣ የማመስገኛ እና የነጻነት ጊዜያቸው ተወዳጅ ባህላዊ ክዋኔ ነው።

“አሱሪቴ” በብሄረሰብ አስተዳደሩ በአንዳንድ አካባቢዎች እየተከበረ የቆየ ተናፋቂ በዓል ሲሆን ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ በሁሉም አካባቢዎች የአደባባይ በዓል ሆኖ በድምቀት ይከበራል።

በዓሉ ከነሐሴ 20_ጳጉሜ 5/2018 ዓ.ም “ባህል ድልድያችን፤አንድነት መዳረሻችን!” በሚል መሪ ቃል
በብሔረሰብ አስተዳደራችን በሚገኙ ቀበሌዎች ጀምሮ እስከ ክልል ድረስ መርሃ-ግብር ተዘጋጅቶለት በድምቀት እንደሚከበር ሀላፊው ገልፀዋል።

አሱሪቲ ዛሬ ነው ወይ፣
እሸት የሚበላው ዛሬ ነው ወይ፣
ውኃ የሚጎድለው ዛሬ ነው ወይ፣
ፀሐይ የምትወጣው ዛሬ ነው ወይ”
የሚሉ ለአዲስ ዓመት ተስፋን የሚያጭሩ ባሕላዊ ዘፈኖችም በበዓሉ ወቅት የሚዘወተሩ ናቸው።






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: