የ22 ዓመታት ጥበቃ አበቃ አዲሱ የትንሣኤ ፊልም ቀጣዩ ምዕራፍ ተበሰረ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የሜል ጊብሰን “The Passion of the Christ” ፊልም ከ20 ዓመታት በኋላ በድጋሚ በሲኒማዎች ሊታይ ነው

በሜል ጊብሰን አዘጋጅነት በፈረንጆቹ በ2004 ተመርቆ ከፍተኛ ተቀባይነትና አድናቆትን ያተረፈው “The Passion of the Christ” የክርስቶስ ሕማማት ፊልም በዘመናዊ ምስልና ድምፅ ጥራት ተሻሽሎ በሲኒማ ቤቶች በድጋሚ እንደሚታይ ተገልጻል።

የፊልሙ በድጋሚ በሲኒማ ቤቶች መታየቱ ዋና ምክንያት የቀጣዩ ክፍል “The Resurrection of the Christ” የክርስቶስ ትንሣኤ መምጣት ነው ተብሏል።

በዚህ በሚቀጥለው መስከረም ወር በሲኒማ ቤቶች በሚለቀቀው የድሮው ፊልም ማጠቃለያ ላይ ስለ አዲሱ ፊልም ከጀርባ የተቀረፁ ልዩ አጫጭር ምስሎች ለተመልካች ይቀርባሉ ነው የተባለው።

አዲሱ ፊልም በሁለት ክፍሎች ተከፍሎ የሚቀርብ ሲሆን ክፍል አንድ በዓለም አቀፍ ሲኒማዎች አማካኝነት እንደሚመረቅ ታውቋል።

በዋናው ፊልም ላይ የኢየሱስ ክርስቶስን ገጸ-ባህሪ ወክሎ የተጫወተው ጂም ካቪዘል በድጋሚ በዚሁ ሚናው እንደሚመለስ ተገልጿል።

ክፍል ሁለት “The Resurrection of the Christ” የክርስቶስ ትንሣኤ መምጣት ፊልም በፈረንጆቹ 2027 ግንቦት ወር ላይ ለእይታ እንደሚበቃ ነው የተገለፀው።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#TheResurrectionChrist
#ThePassionChrist
#MelGibson #cinema


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1