በታይዋን እየተካሄደ ባለው የዓለም የቁንጅና ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክላ በመሳተፍ ላይ የምትገኘው ሚስ ኢትዮጵያ ሩት ይርጋለዓለም፣ የአገሯን ስም በዓለም መድረክ ከፍ ለማድረግ የሚያስችላትን የህዝብ ድምፅ አሰጣጥ (Voting) ሂደት መጀመሩን ገለጸች።
ተወዳዳሪዋ ሩት ይርጋለዓለም ከገጠማት የቤተሰብ ሀዘን ጋር ተያይዞ የመጣውን ፈተና በመቋቋም ውድድሩን በፅናት እያካሄደች እንደምትገኝ የታወቀ ሲሆን፣ አሁን ባለው የውድድር ደረጃ የኢትዮጵያውያን ድጋፍና አንድነት ወሳኝ መሆኑ ተጠቅሷል። የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ይፋ መደረጉን ተከተሎ፣ ደጋፊዎቿ እና የጥበብ አፍቃሪዎች በተዘጋጀው የኢንተርኔት ሊንክ አማካኝነት ድምፅ በመስጠት እና መልእክቱን በማጋራት (Share) አገራዊ አለምአቀፍ ውክልናዋን እንዲያጠናክሩ ጥሪ ቀርቧል።
📍የድምፅ መስጫ ሊንኩን የመጀመሪያው አስተያየት ላይ አስቀምጠናል።
ወደ ሊንኩ ሲገቡ “Category” የሚለውን ይጫኑ፤ በመቀጠል “Africa Round 1” የሚለውን መርጠው “Free Vote” የሚለውን ሲጫኑ የ”1Zone App” አፕሊኬሽን ይመጣል። እሱን ዳውንሎድ በማድረግ በነፃ ድምፅ መስጠት ይችላሉ!




Source: FastMereja







No comments yet.