#Ethiopia | በ117 ዓመታቸው የዓለማችን እድሜ ጠገብ የተባሉት እንግሊዛዊቷ ኤተል ካተርሃም የልደት በዓላቸውን አከበሩ።
በጊነስ የዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ በህይወት ካሉ የዓለማችን እድሜ ጠገብ ሰው በመሆን እውቅና የተሰጣቸው እንግሊዛዊቷ ኤተል ካተርሃም 117ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል።
ኤተል የልደት በዓላቸውን ምክንያት በማድረግ ለኤቢሲ ኒውስ በላኩት የምስጋና መልዕክት “ለተመኛችሁልኝ በጎ የልደት ምኞት ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ ብለዋል።
በ117 ዓመቴ በምድር ላይ ሁሉንም አይቻለሁ ሲሉም ተናግረዋል።
አክለው “ከህጻናት እጅ መዳሰስ እስከ ንጉስ እጅ መያዝ ድረስ በህይወቴ በርካታ ታሪካዊና አስደናቂ ነገሮችን አድርጌያለሁ” ሲሉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1909 የተወለዱት ኤተል ካተርሃም በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያላቸውን ሁለቱን የዓለም ጦርነቶች በርካታ የቴክኖሎጂና የፖለቲካ ውጣ ውረዶችን እንዲሁም በርካታ ታሪካዊ ሁነቶችን በህይወት አሳልፈዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#England #catrinham
#ABCNews #birthday
#worldguinnessrecord
Source: GetuTemesgen








No comments yet.