በአገው ምድር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ28 ዓመታት ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበችው ተማሪ ቤተ መጻሕፍት በስሟ ተ

- Advertisement -
Sidebar AD

በአገው ምድር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ28 ዓመታት ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበችው ተማሪ ቤተ መጻሕፍት በስሟ ተሰየመላት

#Ethiopia | በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር እንጅባራ ከተማ በሚገኘው የአገው ምድር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባለፉት 28 ዓመታት ከተመዘገቡት ሁሉ በላጭ የሆነ የትምህርት ውጤት ተመዝግቧል።

የኢትዮጵያ ሚሊኒየም በገባበት በ2000 ዓ.ም የተወለደችው ተማሪ ህዳሴ ዘመኑ በ11ኛ ክፍል የትምህርት ዘመኗ 99.67 በመቶ ያመጣች ሲሆን ይህም በትምህርት ቤቱ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው ከፍተኛ ውጤት ነው።

በአሁኑ ወቅት የ12ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ህዳሴ ያስመዘገበችውን ድንቅ ውጤት እና ጥረት ለማስከበር ትምህርት ቤቱ ቤተ መጻሕፍቱን በስሟ ህዳሴ ቤተ መጻሕፍት በማለት ሰይሞላታል።

ተማሪ ህዳሴ የተደረገላት እውቅና ለቀጣይ ጥረቷ ትልቅ የመንፈስ ጥንካሬ እንደሆናት ገልጻ ወደፊት በሶፍትዌር ቴክኖሎጂ ዘርፍ በመሰማራት ሀገሯን የማገልገል ትልቅ ራዕይ ሰንቃ በመማር ላይ ትገኛለች።

በሌላ በኩል በትምህርት ሚኒስቴር ይፋ በተደረገው የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ውጤት ከአገው ምድር ትምህርት ቤት በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ በሴቶች 583 ከ600 እንዲሁም በወንዶች 591.6 ከ600 በመመዝገብ ከፍተኛ ውጤት ከተመዘገበባቸው ትምህርት ቤቶች አንዱ ለመሆን ችሏል።

#Education #AcademicExcellence #InspiringStudents #Injibara #AgewMidir #EthiopianStudents #NationalExam #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2