የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 12.82 በመቶ የሚሆኑት ማለፋቸው ተገለጸ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የትምህርት ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ያደረገ ሲሆን ለፈተና ከተቀመጡት ተማሪዎች መካከል 12.82 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ማለፋቸውን አስታውቋል።

የዘንድሮውም ቢሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ ሆኗል።

​በሚኒስቴሩ ገለጻ መሠረት በዘንድሮው የትምህርት ዘመን ለፈተናው ከተመዘገቡት 563 ሺህ 960 ተማሪዎች መካከል 550 ሺህ 210 የሚሆኑት ፈተናውን በአካል ተገኝተው ወስደዋል።

ከእነዚህ ፈተናውን ከተከታተሉት ተማሪዎች ውስጥ 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ማምጣት የቻሉት 70 ሺህ 544 ያህሉ ብቻ ናቸው።

​የተመዘገበው ውጤት በተፈጥሮ ሳይንስ እና በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፎች መካከል ጎልቶ የሚታይ ልዩነት አሳይቷል።

በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ፈተናውን ከወሰዱት ተማሪዎች ውስጥ 16.5 በመቶ ያህሉ ማለፍ ሲችሉ፣ በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ደግሞ ማለፍ የቻሉት 8.33 በመቶ ተማሪዎች ብቻ እንደሆኑ ተገልጿል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: