ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሲሌሲያ ዳይመንድ ሊግ አብላጫውን የበላይነት ተቀዳጁ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በፖላንድ በተካሄደው የሲሌሲያ ዳይመንድ ሊግ ውድድር አትሌት ገመቹ ጎዳና በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል እንዲሁም አትሌት ፅጌ ድጉማ በ1500 ሜትር አሸናፊ በመሆን የደመቀ ድል አስመዝግበዋል።

በወንዶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ውድድር አትሌት ገመቹ ጎዳና ርቀቱን በ8 ደቂቃ ከ02 ሰከንድ በማጠናቀቅ የመጀመሪያ ደረጃን ይዟል።

አትሌቱ የዓለምና የኦሊምፒክ ሻምፒዮን የሆነውን ሞሮኮአዊ አትሌት ሱፊያን ኤል ባካሊን በማስከተል ነው ቀዳሚ መሆን የቻለው።

በሴቶች 1500 ሜትር ውድድር የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮኗ ፅጌ ዱጉማ 3 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ በሆነ ፈጣን ጊዜ በመግባት የውድድሩ አሸናፊ ሆናለች።

በዚሁ ርቀት የተካፈሉት አትሌት ብርቄ ኃየሎም 8ኛ እንዲሁም አትሌት ሳሮን በርሄ 11ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።

በሌላ በኩል 8 ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተሳተፉበት የሴቶች 5 ሺህ ሜትር ሩጫ አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ 14 ደቂቃ ከ54 ሰከንድ በሆነ ጊዜ ጣሊያናዊቷን ናዲያ ባቶክሌቲን ተከትላ 2ኛ ደረጃን በመያዝ ጨርሳለች።

#SilesiaDL #DiamondLeague #Athletics #EthiopianAthletes #GemechuGidana #TsigeDuguma #FreweyniHailu #EthiopianSport #Running #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: