ጋዜጠኛ፣ ደራሲ እና ገጣሚ መስፍን አራጌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በኢትዮጵያ የሚዲያ እና የሥነ ጽሑፍ ዘርፍ ለረጅም ዓመታት በታማኝነት እና በከፍተኛ ሙያዊ ብቃት ሲያገለግሉ የቆዩት ታዋቂው ጋዜጠኛ፣ ደራሲ እና ገጣሚ መስፍን አራጌ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እንገልጻለን።

በ1965 ዓ.ም የተወለዱት ጋዜጠኛ መስፍን አራጌ፣ ከ1988 እስከ 2018 ዓ.ም ባሉት ሦስት አሥርት ዓመታት ውስጥ በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የደሴ ቅርንጫፍ፣ በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዲሁም በአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የደሴ አካባቢ ተወካይ በመሆን በጋዜጠኝነት እና በስቱዲዮ አስተባባሪነት የሕዝብ ድምፅ ሆነው አገልግለዋል።

ከጋዜጠኝነት ሥራቸው በተጨመሪ በርካታ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎችን ለንባብ ያበቁት ደራሲ እና ገጣሚ መስፍን አራጌ፣ ባለ ትዳር እና የአንድ ልጅ አባት ነበሩ።

የጋዜጠኛው የስንብት ሥነ ሥርዓት ዛሬ በርዕሰ አድባራት ደሴ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ይፈጸማል።

ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸው እንዲሁም ለመላው የአንባቢና የአድማጭ ማኅበረሰብ መጽናናትን እንመኛለን።

#dessie #fanafm #ethiopiannews #journalism #literature #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2