#Ethiopia | ታሪካዊው “ባልቻ አባ ነፍሶ” ቲያትር በትውልድ አካባቢያቸው ወሊሶ ከተማ ሊቀርብ ነው!
የታሪካዊው “ባልቻ አባ ነፍሶ” ተውኔት ቡድን አባላትና ጋዜጠኞች የጀግናው ደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶ ቲያትር ለማስመልከት ወሊሶ ከተማ ገብተዋል።
ይህ ታሪካዊ ቲያትር በወሊሶ ከተማ ለሚገኙ ተመልካቾች የሚቀርበው የአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ከወሊሶ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር ባዘጋጀው መርሃ ግብር እንደሆነ ታውቋል።
“ባልቻ አባ ነፍሶ” ዘወትር እሁድ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ ለተመልካች የሚቀርብ ዝነኛ ትያትር ነው።
ዛሬ በጀግናው ትውልድ ከተማ ለወሊሶና ለአካባቢው ነዋሪዎች በልዩ ሁኔታ እንደሚቀርብ ተገልጿል።
የወሊሶ ከተማና የአካባቢው ነዋሪዎች በሙሉ ታሪካዊውን ተውኔት በአካል ተገኝተው እንዲመለከቱ ጥሪ ቀርቧል።
የጀግናውን የደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶን ገድልና ታሪክ የሚያሳየው ድንቅ ትያትር ለወሊሶ ከተማ ነዋሪዎች የሚቀርብ ይሆናል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
Source: GetuTemesgen







No comments yet.