ንቃተህሊና (ዮሐንስ ምስክር) በMMA Adwa Fight ድል አበሰረ!

- Advertisement -
Sidebar AD

🥊

#Ethiopia | የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የቡና መገኛ ምድር ካፋ ፍሬ የሆነው ንቃተህሊና፣ በዛሬው ETFC 02 የድብልቅ ማርሻል አርት (MMA) ውድድር ከተጋጣሚው ሮቤል ገብረስላሴ ጋር ያደረገውን አሰደናቂ ፍልሚያ በከፍተኛ ብቃት በአሸናፊነት አጠናቋል!

የፅናት ውጤት፡
በETFC 01 ያመለጠውን አጋጣሚ በስፖርታዊ ጨዋነትና በትጋት በማስተካከል፤ የሚዲያ ጫናዎችን በረጋ መንፈስ ተቋቁሞ ለዛሬው ድል በቅቷል።

የስፖርቱ አለኝታ፡
የMMA ስፖርት በሀገራችን አደባባይ እንዲወጣና ተገቢውን ቦታ እንዲይዝ በድፍረት የታገለ የቁርጥ ቀን ልጅ።

በኬጁ ውስጥ እጅን በአፍ የሚያስጭን ውብ እንቅስቃሴ በማሳየት የክልሉና የሀገሩ ኩራት መሆኑን አስመስክሯል።

እንኳን ደስ አለህ!
ድል ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ካፋ ዞን!

#MMA #ETFC02 #AdwaFight #NqateHilina #Ethiopia #Kaffa





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1