#Ethiopia | በኢትዮጵያ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ምርት ዘርፍ በስፋት እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ሳሬም ፈርኒቸር ሦስተኛ አዲስ ቅርንጫፉን መክፈቱን አስታወቀ።
ተቋሙ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የሚዲያ አካላት፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የይዘት ፈጣሪዎች በተገኙበት ባካሄደው የምርቃት ሥነ ሥርዓት የአገር ውስጥ የማምረት አቅምን ማሳደግና ጥራት ያላቸውን ምርቶች በፍትሃዊ ዋጋ ለደንበኞች ማቅረብ ቀዳሚ ዓላማው መሆኑን ገልጿል።
የድርጅቱ ተወካዮች በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር የዚህ ቅርንጫፍ መከፈት ለቀጣይ የዕድገት ጉዞ አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት ጠቁመዋል።
ሳሬም ፈርኒቸር የጥንካሬ፣ ዘላቂነት፣ ምቾትና ውበት እሴቶችን መሠረት በማድረግ የሚሠራ በመሆኑ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካትና ተጨማሪ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር እየሠራ እንደሚገኝ ተብራርቷል።
ወደፊትም በአገር ውስጥ ተጨማሪ ቅርንጫፎችን ከመክፈት ባሻገር በክልሉና በአህጉር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ ዕቅድ እንዳለው ተገልጿል።
በሥነ ሥርዓቱ ማጠቃለያ ላይ ለተቋሙ ዕድገት አስተዋጽኦ ላደረጉ ደንበኞች፣ ለሥራ ባልደረቦችና ለሚዲያ አጋሮች ምስጋና የቀረበ ሲሆን አዲሱ ቅርንጫፍ ከዛሬ ጀምሮ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ ተበስሯል።
#SaremFurniture #FurnitureEthiopia #LocalManufacturing #BusinessNews #EthiopianBusiness #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa




Source: GetuTemesgen







No comments yet.