#Ethiopia | ተመድ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዘረኝነት ላይ የሚደረገው ትግል እንዲጠናከር ጥሪ አቀረበ።
ዘረኝነት በአለም አቀፍ ደረጃ በሰዎች እኩልነት እና ሰብአዊ መብት ላይ ከፍተኛ አደጋ ደቅኖ እንደሚገኝ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።
ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው ዘረኝነት አሁንም ድረስ በስፋት በሚታዩ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እኩልነት ማጣቶች ሰዎችን ከማህበረሰብ ከመግለል እንዲሁም በዜጎች ላይ በሚፈጸሙ ጥቃቶች እና በደሎች አማካኝነት በተለያየ መልኩ ይገለጻል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ባስተላለፉት ጥብቅ መልእክት፣ ዘረኝነት ሁላችንም በጋራ ልንታገለው እና ልንቃወመው የሚገባ አጸያፊ ድርጊት መሆኑን አሳስበዋል።
ዋና ጸሐፊው አክለውም፣ በዘረኝነት ድርጊቶች ላይ ዝምታን መምረጥ እና አለመናገር ድርጊቱ ይበልጥ እንዲስፋፋ እና ስር እንዲሰድ መንገድ እንደሚከፍት ገልጸዋል።
ዘረኝነትን ማስወገድ የአንድ ጊዜ መግለጫ ወይም አቋም በመያዝ ብቻ የሚያበቃ አለመሆኑ የተገለጸ ሲሆን ተቋማት እና ግለሰቦች ድርጊቱን ለማጥፋት የዕለት ተዕለት ቁርጠኝነት ሊኖራቸው እንደሚገባ ተጠቁሟል።
በመጨረሻም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰብአዊ መብቶችን ለማስከበር እና ዘረኝነትን ለማጥፋት በሚደረገው ዓለም አቀፍ ትግል ላይ ማንኛውም አካል የራሱን ድርሻ እንዲወጣ እና በጽናት እንዲቆም ጥሪውን አስተላልፏል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#unaited #nation
#racism #politics
#policy #secretary
Source: GetuTemesgen







No comments yet.