አረጋዊያኑ ለፖሊስ ያደረሱት አስደንጋጩ የስልክ ጥሪ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በጣሊያን ነዋሪነታቸው ያደረጉት ባልና ሚስት ፖሊስ በፍጥነት ይድረስልን ሲሉ ጥሪ አድርሰዋል።

ጥንዶቹ ወደ ፖሊስ ጣቢያ የደወሉት ወንጀል ተፈጽሞባቸው ወይም አደጋ አጋጥሟቸው አልነበረም።

ይልቁንም የስልክ ጥሪ ያደረጉት በከባድ ብቸኝነት እና የባዶነት ስሜት በመጨነቃቸው ምክንያት ነበር።

እሳቸውና ባለቤታቸው በዕድሜ የገፉ በመሆናቸው በሥነ ልቦናዊ ሁኔታቸው ተጎድተው የነበረ ሲሆን ችግራቸውን የሚነግሩትና የሚያናግሩት የቅርብ ሰው በማጣታቸው ለፖሊስ ለመደወል ተገደዋል።

ፖሊሶቹ አረጋውያኑ ዘንድ ደርሰው ሁኔታውን ሲያጣሩ ምንም ዓይነት አስቸኳይ የወንጀል ወይም የሕክምና አደጋ አለመኖሩን ተረዱ።

ምንም ዓይነት ወንጀል አልተፈጸመም፣ የነፍስ አድኖ ሥራ አልተከናወነም ወይም የተጋነነ የጀግንነት ድርጊት አልነበረም።

ይልቁንም ሁለት የፖሊስ አባላት አንዳንድ ጊዜ ከሁሉ በላይ ትልቁና ትርጉም ያለው እርዳታ የሰው ልጅ አጋርነትና የቅርብ ወዳጅነት መሆኑን ተረድተው መተግበራቸው ብቻ ነው።

የጣሊያን ባለሥልጣናት እንደገለጹት የፖሊስ ዋና ተግባር ሕግ ማስከበር ቢሆንም ድጋፍ የሚሹ ዜጎችን በማኅበራዊ አገልግሎት መደገፍም የደኅንነት ጥበቃው አካል እንደሆነ አሳውቀዋል።

ታሪኩ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ትኩረት ሊያገኝ የቻለው በበለጸጉ ሀገራት ዘንድ የማኅበራዊ ብቸኝነት ትልቅ የሕዝብ ጤና ስጋት እየሆነ በመምጣቱ ነው።

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በአረጋውያን ላይ የሚታይ የረጅም ጊዜ ብቸኝነት ለድብርት፣ ለከባድ የአእምሮ ማሰብ አቅም መቀነስ ለልብ ሕመም እና ለሞት የመጋለጥ እድልን ያፋጥናል።

ይህ ክስተት በሰው ልጅ አእምሮ ውስጥ ታስቦ እንዲቀር ያደረገው ደግሞ የፖሊሶቹ ቀናነት ነው።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#Italy #police #phone
#calls #worldoddnews
#Crimes #women


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2