ዩጎ ሲቲ ቸርች ቦሌ አጥቢያ ላይ ትልቅ የአምልኮ ፕሮግራም ሊካሄድ ነው!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Fastmereja I ሙዚቀኛውና የአምልኮ ፕሮግራም አዘጋጁ ዮሐንስ ዋጋሪ ከአሜሪካና ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የአምልኮ መድረኮች ቆይታ በኋላ፣ በኢትዮጵያ ታላቅ የአምልኮ ፕሮግራም ለማዘጋጀት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን በዛሬዉ እለት በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንደተገለጸው፣ ይህ ፕሮግራም ከአንጋፋና ከአዳዲስ ዘማሪዎች ጋር በመቀናጀት የተዘጋጀ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም የወንጌል ስርጭትን ማስፋፋትና አምልኮን ማቅረብ መሆኑ ተገልጿል።

ዮሐንስ ዋጋሪ ቀደም ሲል በአሜሪካ 18 ስቴቶች እንዲሁም በአውስትራሊያና በሌሎች ሀገራት ተመሳሳይ ፕሮግራሞችን ሲያዘጋጅ የቆየ ሲሆን እድሉ የሌላቸውን አዳዲስ ዘማሪዎችና ባለጸጋዎችን በነፃ በስቱዲዮ በማስተናገድና በመደገፍ ይታወቃል።

ይህ የአምልኮ መድረክ በከፍተኛ ጥራትና የላቀ ዝግጅት (Excellence) የሚቀርብ ሲሆን፣ የቃሉን አገልግሎት የሚያካፍሉ አገልጋዮችም አብረው እንደሚሳተፉም ነዉ የተገለፀዉ።

የዜማ ዮሐንስ ፕሮጀክት (Zema Yohannes Project) ከተጀመረ ከ10 ዓመታት በላይ እንሆነዉ የተገለፀ ሲሆን በወጣቶች ላይ ትኩረት አድርጎ አዳዲስ ዘማሪዎችን እንደሚያበራታ እና የወንጌል ስርጭት ስራዎችን እንደሚሰራ ገልጿል።

#ኹነት






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: