የኢትዮጵያ አየር መንገድ እስከ 10 የቦይንግ የጭነት አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከስምምነት ሊደርስ ነውእንደ አሜሪካ ጆርናል ኦፍ …

- Advertisement -
Sidebar AD
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እስከ 10 የቦይንግ የጭነት አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከስምምነት ሊደርስ ነው
እንደ አሜሪካ ጆርናል ኦፍ ትራንስፖርቴሽን ዘገባ መሰረት ​የኢትዮጵያ አየር መንገድ እስከ 10 የሚደርሱ ቦይንግ የጭነት አውሮፕላኖችን ለመግዛት የሚያስችለውን ስምምነት ለማጠናቀቅ መቃረቡን ምንጮች ገለጹ።
ይህ ውል አየር መንገዱ ከአረብ ኤምሬትስ እና ቀጣናው አየር መንገድ ኩባንያዎች ጋር ያለውን ውድድር ለማጠናከር እና አዲስ የአፍሪካ የአየር ትራንስፖርት ማዕከል  ለመገንባት ለያዘው እቅድ ትልቅ ማበረታቻ ነው ተብሏል።
​እንደ ዘገባው ከሆነ፣ ግዢው ሁለት የነባሩን ‘777F’ ሞዴል እና የተቀሩትን ደግሞ አዲስ ምርት የሆኑትን ‘777-8F’ የጭነት አውሮፕላኖች ያካተተ ነው።
ቦይንግ የ ‘777X’ አውሮፕላን ማረጋገጫ በመዘገየቱ ምክንያት ነባሩን ሞዴል የማምረት ፈቃድ ለማራዘም ከአሜሪካ አቪዬሽን ባለስልጣን ጋር እየተነጋገረ ይገኛል።
​አየር መንገዱ እና ቦይንግ በጉዳዩ ላይ እስካሁን የሰጡት ይፋዊ አስተያየት ባይኖርም፣ ውሉ አየር መንገዱ በዓለም አቀፍ የካርጎ ኤክስፖርት አገልግሎት ያለውን የበላይነት የበለጠ እንደሚያጠናክረው ተገልጿል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1