ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል”ህወሓት እና ፋኖ ተስማምተው 10 ኪሎ ሜትር እንኳን አብረው መሄድ አይችሉም…

- Advertisement -
Sidebar AD
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል
“ህወሓት እና ፋኖ ተስማምተው 10 ኪሎ ሜትር እንኳን አብረው መሄድ አይችሉም! ፕሮፌሰር ብረሃኑ ነጋ”
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ፣ በቅርቡ “ስለ ጽምዶ” ያሏቸውን ምልከታ አጋርተዋል።
ሚኒስትሩ በንግግራቸው፦
፩. “ህወሓት እና ፋኖ ተስማምተው 10 ኪሎ ሜትር እንኳን አብረው መሄድ የሚችሉ አይመስለኝም” ሲሉ የኃይሎቹን ህብረት አጫጭር እና የማይዘልቅ ሲሉ ገልጸውታል።
፪. “በጽምዶ ስም የተሰባሰቡት አካላት መሠረታዊ የርዕዮተ-ዓለም እና የፖለቲካ ዓላማ ልዩነት ስላላቸው፣ የፈጠሩት ጥምረት የትም ሊደርስ እንደማይችልና ውጤት እንደማያመጣ አስረድተዋል።
፫. እንዲህ ዓይነቶቹ ጊዜያዊ ጥምረቶች በሀገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር ላይ ዘላቂ ለውጥ ማምጣት እንደማይችሉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
የፕሮፌሰር ብርሃኑ አስተያየት በሀገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች እና በተቃዋሚ ኃይሎች ጥምረት ላይ የመንግሥትን አቋም የሚያንጸባርቅ እንደሆነ ተመልክቷል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: