#Ethiopia | የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የፓንደሚክ ፈንድ የበላይ ቦርድ ተባባሪ ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።
የፓንደሚክ ፈንድ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸዉ አገራትን አቅም በመገንባት ድንገተኛ የጤና አደጋ ክስተቶችን ለመከላከል፣ ለመለየትና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እንዲቻል በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተቋቋመ መሊቲላተራል ፋይናንሲንግ አሰራር ሲሆን ሚኒስትሯ በአዲሱ ኃላፊነታቸው ዓለም አቀፍ አጋርነቶች እንዲጠናክር እና አገራት ወረርሽኞችን ለመከላከል ለሚያደርጉት ኢንቨስትመንት የሚሰጠውን ድጋፍ በበላይነት በመምራት ለዉጥ እንደሚያመጡ ፈንዱ ያለዉን እምነት ገልጸዋል፡፡
ዶ/ር መቅደስ ኃላፊነቱን የተረከቡት ከሩዋንዳ ጤና ሚኒስትር ከሆኑት ከዶ/ር ሳቢን ንሳንዚማና ሲሆን፣ ሚኒስትሯ ባስተላለፉት መልዕክት የህብረተሰባችንን ህይወት መታደግ የሚችልና የዓለምን የጤና ደህንነት ዋስትናን የሚያረጋግጥ ጠንካራ የጤና ስርዓት በመገንባት ለትዉልድ ማስተላለፍ አለብን ብለዋል።
Credit : ጤና ሚኒስቴር
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.