የባህል አምባሳደሩ አርቲስት ሰማህኘ በለው ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ይታወሳል !

- Advertisement -
Sidebar AD

የጎጃም ግሸ አባዩ ፈርጥ :
የባህል አምባሳደሩ : የሀገር ባለውለታው ሁለገቡ አርቲስት ሰማህኘ በለው ተወልዶ ባደገባት ገፅታዋንም በጥበብ ስራው ሲገነባት በኖረው ባህር ዳር ከተማ ይዘከራል ::

የአርቲስቱ የልጀነት ጓደኞች : ቤተሰቦች : የጥበብ ቤተሰቦች እና አድናቂዎች በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ የክብር ስንብትና የምስል ሃዘን ዝግጅት ይታወሳል ።

የዝግጅቱ ዋና አስተባባሪ ፕሮሞተር ደመወዝ ገነቱ መርዓ ግብሩ እንደሚከተለው መዘጋጀቱን ገልፆል ።

የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ የሃዘን ስሜቱን በሚገልጽ አለባበስ (ጥቁር በመልበስ) ከጠዋቱ 2:00 ላይ በባህር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት፣ ከአዲስ አበባ የሚመጡትን የሟችን ባለቤት ወይዘሮ ገበያነሽ አባተ እና ልጁ ቢኒያም ሰማኸኝን ጨምሮ የሟች ጓደኞቹን ይቀበላል ።

​የከተማዋ ነዋሪ በቀድሞው አፄ ቴዎድሮስ ስታዲየም ወይም በጃካራንዳ ሆቴል ፊት ለፊት ቅዳሜ ጠዋት 2:30 ሰዓት ላይ ይሰበሰባል።

ነዋሪው የሟች ቤተሰቦችና እንግዶች በማርሽ ባንድ በሃዘን ዝግታዊ ድባብ ታጅበው በከፍተኛ የሃዘን ድባብ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያንና ወደ አደባባዩ የሚወስደውን የክብር ጉዞ ያደርጋሉ።

​በባህር ዳር ከተማ ህዝብ ጥንታዊና ጥልቅ የልቅሶ ባህል፣ ወግና ስርዓት መሠረት፣ ለታላቁ አርቲስት ሰማኸኝ በለው ልብን የሚነካና የህዝብን ስብራት የሚገልጽ የሙሾና የልቅሶ ስነ-ስርዓት ይከናወናል።

የባህል ​የኪነ-ጥበብ ሰማይ ኮከብ የነበረው የአርቲስት ሰማኸኝ በለው፣ ለሀገርና ለወገን ያበረከተው ታላቅ አስተዋጽኦ፣ ያሳለፈው ውጣ ውረድና አጠቃላይ የህይወት ታሪኩ ለሃዘንተኛው ይነበባል።

ውድ ህይወቱን ለጥበብ በሰጠው አርቲስት መታሰቢያ ላይ፣ በሀገር ታዋቂ ሰዎች፣ የስራ ባልደረቦቹ፣ ቤተሰቦቹና ጥልቅ ሃዘን በገባቸው አድናቂዎቹ አማካኝነት የክብር የአበባ ጉንጉን ይቀመጣል።

​የሟች ነፍስ በሰላም እንድታርፍ፣ በሃይማኖቱ መንፈሳዊ ህግና ስርዓት መሠረት ታላቅ የፍትሃት ጸሎት በሃይማኖት አባቶች ይመራል።

ስለ አርቲስት ሰማኸኝ በለው መልካምነት፣ ሰብዓዊነትና ታላቅነት በህይወት በነበረበት ጊዜ አብረውት የነበሩ የቅርብ ወዳጆቹ፣ የሙያ አጋሮቹ፣ የቤተሰብ አባላትና የልብ ጓደኞቹ ልብ የሚነካ ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ።

እንዲሁም ሌሎች የአዳራሽ ልዪ ልዪ ፕሮግራሞች እንደሚኖሩ ታውቋል

መላው የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ ለአርቲስቱ
የመጨረሻውን ክብር እንድትሰጡ ኮሚቴው ጥሪውን ያስተላልፋል።

​”የጥበብ ሰው አይሞትም፣ በስራዎቹ ሁልጊዜም በልባችን ይኖራል!”

ኮሚቴው…


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: