*በዕድሜ ትንሹ ባንክ የትልቅ ሕንጻ ባለቤት ሆነ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ሥራ ከጀመረ 3ኛ ዓመቱ ላይ የሚገኘው አሐዱ ባንክ የ15 ፎቅ ባለቤት ለመሆን ችሏል፡፡

ምንጮቻችን እንደነገሩን፤ ባንኩ ሕንጻውን በጨረታ የገዛው፤ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው የሐራጅ ጨረታ ላይ በመወዳደር ሲሆን፤ ሌሎች ተጫራጮች ለግዥ ካቀረቡት ክፍያ ከፍ ያለውን በማቅረብ አሸናፊነቱ በመረጋገጡ ነው፡፡

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክም አሀዱ ባንክ ያቀረበውን ከፍተኛ ዋጋ እንደተቀበለው እነዚሁ ምንጮች ለሚድያችን አረጋግጠው፤ ሕንፃውም ከመሬት በታች ባለ 2 ቤዝመንት እንዲሁም ከመሬት ደግሞ የ15 ፎቆች ከፍታ ያለው መሆኑን ታማኝ ምንጮቻችን ነግረውናል፡፡

ሕንጻው ግንባታው በከፊል የተጠናቀቀ ሲሆን፤ የሚገኝበት ቦታ ደግሞ አዲስ አበባ፣ ሜክሲኮ አካባቢ መሆኑን አውቀናል፡፡

ይህ ግዥ ባንኩ በተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ የራሱ ሕንፃ እንዲኖረው ያስችለዋል፡፡


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2