“መርጌታ ነኝ እቁብ እንዲደርስህ አደርጋለሁ” በማለት 625 ሺህ ብር ያጭበረበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለገንዘቡን የተጭበረበ…

- Advertisement -
Sidebar AD
“መርጌታ ነኝ እቁብ እንዲደርስህ አደርጋለሁ” በማለት 625 ሺህ ብር ያጭበረበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ‼️
ገንዘቡን የተጭበረበረው ግለሰብ በደረሰበት የሥነ ልቡና ቀውስ ፀበል ገብቶ ነበር። አብርሀም ሰርኬ የሚባለው ግለሰብ በሐሰት መር ጌታ ነኝ በማለት  አቶ ደነቀው ሙሉቀን ከተባለና በዳንሻ ከተማ  በሆቴል ስራ ላይ ከተሰማራ  ግለሰብ 625ሺህ ብር አታሎ መውሰዱን የሉማሜ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አዛዥ ኢንስፔክተር በድሉ መልሰው ተናግረዋል።
ወንጀሉን የፈፀመው ግለሰብ “እቁብ እንዲደርስህ አደርጋለው” በማለት ታህሳስ 2018ዓ.ም  ብሩን አታሎ መስዷል።
ይህን ብር ከወሰደ በኋላ በተጨማሪ ሦስት መቶ ሺህ ብር ካልጨመረክ “ቤተሰብህን በሙሉ በመተት አጠፋብሃለው” በማለት በተበዳይ ላይ አደገኛ የማጭበርበር ወንጀል ሲፈፅም መቆየቱ ተመላክቷል።
የዳንሻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት የፍ/ቤት መያዥያ ትዕዛዝ በማውጣት ተጠርጣሪው በተገኘበት በቁጥጥር ስር እንዲውል በፃፈው የትብብር ደብዳቤ ከምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የመረጃ ክትትል ቡድን ጋር በመተባበር ግለሰቡ ሰኔ 15/2018 ዓ.ም በሉማሜ ከተማ አስተዳደር በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጎል።
አቶ ደነቀው ሙሉቀን  በደረሰበት የማታለል ወንጀል ምክንያት ለከፍተኛ አምዕሮዊ ሥነልቦናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ተጋልጦ በፀበል ቦታ እንደቆየ ተሰምቷል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: