የመዳረሻ ልማት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ባሌ፣ ሮቤ – የኢትዮጵያ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ የመዳረሻ ልማት ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሽግግር፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ማሳደግ ወሳኝ ሚና እንዳለው ገለጹ።

በመዳ ዋላቡ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው 2ኛው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ “The Responsible AI Revolution: Building Ethiopia’s Institutional Edge in Tourism and Hospitality by 2030” በሚል አበይት ርዕስ ሚኒስትሩ “የመዳረሻ ልማት ብሔራዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች” በሚል ርዕስ ባቀረቡት ንግግር፣ መዳረሻዎች የቱሪዝም መስህቦች ብቻ ሳይሆኑ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የኢንቨስትመንት ማዕከላት፣ የማህበራዊ ለውጥ መድረኮች እና የብሔራዊ ማንነት መገለጫዎች መሆናቸውን አስታውቀዋል።

እንደ ዶ/ር አብርሃም ገለጻ፣ ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሞቿ ውስጥ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግ፣ ኢንቨስትመንት ለመሳብ፣ መሠረተ ልማትን ለማዘመን እና ዘላቂ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር እየሰራች ሲሆን፣ የመዳረሻ ልማት እነዚህን ግቦች በተግባር የሚያሳካ ስትራቴጂ መሆኑን ጠቁመዋል።

ሶፍ ኦማር ዋሻዎች፣ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፣ ዋንጪ፣ ሐረር፣ ሐዋሳ ሐይቅ፣ ጣና ሐይቅ፣ ገራልታ እና አርባምንጭን ጨምሮ የኢትዮጵያ መዳረሻዎች ጎብኚዎችን፣ ባለሀብቶችን፣ ተመራማሪዎችን እና ፈጣሪዎችን ከዓለም ዙሪያ ለመሳብ ትልቅ አቅም እንዳላቸውም ተናግረዋል።

ዶ/ር አብርሃም የመዳረሻ ልማት በትራንስፖርት፣ ሎጂስቲክስ፣ ግብርና፣ ሪል እስቴት፣ መስተንግዶ እና አገልግሎት ዘርፎች የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን እንደሚያነቃቃ ገልጸው፣ በተለይም ለወጣቶችና ለሴቶች ሰፊ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር አስታውቀዋል።

በተጨማሪም የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያን ጨምሮ በትስስር እና መሠረተ ልማት ላይ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች የቱሪዝም፣ የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና የሪል እስቴት ዕድሎችን እንደሚያሰፉ ገልጸዋል።

በመጨረሻም የኢትዮጵያ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የልማት አጋሮች፣ የግሉ ዘርፍ ባለሀብቶች እና የአካባቢ ማህበረሰቦች በመዳረሻ ልማት ዘርፍ በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበው፣ የኢትዮጵያ መዳረሻዎችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የኢንቨስትመንትና የፈጠራ ማዕከላት ማድረግ እንደሚቻል አስገንዝበዋል።

#Ethiopia #DestinationDevelopment #Tourism #Investment #EconomicGrowth #GetuTemesgen
#Ethiopia #Bale #Tourism #GetuTemesgen #ጌጡተመስገን #ArtificialIntelligence #DigitalEthiopia2030 #MWU






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: