#Ethiopia | ታዋቂው ኢትዮጵያዊ የይዘት ፈጣሪ አቤል ብርሃኑ (የወይኗ ልጅ) ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግሥት የ10 ዓመት የጎልደን ቪዛ ሽልማት ማግኘቱን ይፋ አደረገ።
አቤል ይህንን ከፍተኛ ዕውቅና ያገኘው በይዘት ፈጠራ ዘርፍ ባለው ያለተቋረጠ ጉዞ ሲሆን ይህ የረጅም ጊዜ ቪዛ ወደፊት ለሚሰራቸው ዓለም አቀፍ የጉዞ ዶክመንተሪዎች እና ሌሎች ተያያዥ ሥራዎች ወርቃማ እድል እንደሆነ ገልጿል።
ዓለምን የመዞር የልጅነት ሕልሙን እውን እያደረገ የሚገኘው አቤል፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከሀገሩ ወጥቶ ዓለምን ማሰስ ሲጀምር የተጓዘባት ሁለተኛዋ ሀገር እንደነበረች አስታውሷል።
ለዚህ ታላቅ ስኬት መሳካት መንገዱን ላቀናለት ልዑል እግዚአብሔር ምስጋናውን ያቀረበው የይዘት ፈጣሪው ከጀርባው በመሆን ለደከሙለት፣ በማኅበራዊ ሚዲያ ሥራዎቹን ዘወትር ለሚከታተሉ አድናቂዎቹ እንዲሁም ይህንን ዕድል ለሰጠው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግሥት የላቀ ምስጋናውን አቅርቧል።
”ሽልማቱ እና ስኬቱ የእናንተም ጭምር ነው” በማለት ደስታውን ከመላው ተከታይ ቤተሰቦቹ ጋር የተጋራው አቤል አሁንም የዓለም የማሰስ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.