እንግሊዝ እና ጋና ያለ ግብ ተለያዩ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በ2026 የዓለም ዋንጫ የምድብ 12 ሁለተኛ ጨዋታ፣ እንግሊዝ እና ጋና በቦስተን ስታዲየም ያደረጉት ፉክክር 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታቸውን በድል የጀመሩት ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች በዚህ ጨዋታ ነጥብ በመጋራት ወደ 4 ነጥብ ከፍ ብለዋል።

እንግሊዝ በተለይም በጨዋታው የመጨረሻ ደቂቃዎች ተደጋጋሚ የግብ ሙከራዎችን ብታደርግም፣ የጋናን ጠንካራ መከላከል እና የግብ ጠባቂውን ጥሩ ብቃት ተሻግራ ግብ ማስቆጠር አልቻለችም።

በዚህ ውጤት እንግሊዝ በ4 ነጥብ የምድቡን መሪነት ስትይዝ፣ በካርሎስ ኪሮሽ የምትመራው ጋናም በተመሳሳይ 4 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።

የሁለቱም ቡድኖች ወደ ጥሎ ማለፍ ለማድረስ ያላቸው ዕድል አሁንም ጠንካራ ሲሆን፣ የመጨረሻው የምድብ ጨዋታ ውጤት የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ እንደሚወስን ይጠበቃል።

#WorldCup2026 #England #Ghana #ThreeLions #BlackStars #Football #FIFAWorldCup ⚽🏆


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: