ለኮንስትራክሽን ዘርፍ ቀን ሰራተኞችበኮንስትራክሽን ዘርፍ ለቀን ሠራተኞች የብቃት ማረጋገጫ አስገዳጅ ሊሆን ነውይህ መመሪያ በሰራ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ለኮንስትራክሽን ዘርፍ ቀን ሰራተኞች‼️
በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለቀን ሠራተኞች የብቃት ማረጋገጫ አስገዳጅ ሊሆን ነው

👉ይህ መመሪያ በሰራተኛች ብቃት ማነስ ምክንያት በንብረት እና በግንባት ጥራት ላይ የሚደርስን ችግር ለመቀነስ ነው ተብሏል።

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር በኮንስትራክሽን ዘርፍ እየታየ ያለውን የጥራትና የደህንነት ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል አዲስ መመሪያ በማዘጋጀት ላይ መሆኑን አስታውቋል።
​ይህ አዲስ መመሪያ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎችን ብቻ ሳይሆን፣ ዕለት ተዕለት የሚሰሩ የቀን ሠራተኞችንም የብቃት ደረጃ ማረጋገጥን ግዴታ የሚያደርግ ነው። ሚኒስቴሩ በዘርፉ የተሻለ ጥራትና ደህንነትን ለማስፈን እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጿል።
​እንደ አዲሱ መመሪያ ዝርዝር ሁኔታ፡-
📌​በየትኛውም የግንባታ ቦታ ላይ ለመስራት የሚፈልጉ ባለሙያዎች እና የቀን ሠራተኞች የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መያዝ ግዴታ ይሆናል።
📌​ሕጋዊ የሰርተፊኬሽን ሥርዓት ያላሟላ እና ብቃቱ ያልተረጋገጠ ማንኛውም ባለሙያ ወይም ሠራተኛ በኮንስትራክሽን ሥራ ላይ እንዳይሳተፍ ሙሉ በሙሉ ይከለከላል።
📌​መመሪያው ሙሉ በሙሉ ሕግ ሆኖ ወደ መሬት ወርዶ ተግባራዊ እስኪሆን ድረስ የተወሰኑ ዓመታት ሊወስድ ይችላል።
📌 ​በአሁኑ ወቅት ግን የዚህ አሠራር የቅድመ ዝግጅት እና የሙከራ እንቅስቃሴዎች በይፋ መጀመራቸው ተገልጿል።
​የዚህ አሠራር ዋና ዓላማ የግንባታ ሥራዎችን ጥራትና የሥራ ደህንነትን በአስተማማኝ ሁኔታ ማሻሻል መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2