በኢትዮጵያ የሥነ-ጽሑፍ፣ የሚዲያ እና የኪነ-ጥበብ ዘርፍ ውስጥ ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ በጎ ተጽዕኖ ያሳደረችው ታዋቂዋ ደራሲ፣ ጋዜጠኛ እና ተርጓሚ ኢየሩሳሌም ነጋ፣ #አሎንባኮት” የተሰኘ አዲስና ልብ አንጠልጣይ ረዥም ልብ-ወለድ መጽሐፍ በቅርቡ ለንባብ ልታበቃ መሆኑን አስታወቀች።
ይህ አዲስ ስራ ደራሲዋ ቀደም ሲል ለንባብና ለአድማጭ ካበቃቻቸው በርካታ የፈጠራ ስራዎች ቀጥሎ የተሰናዳ ሲሆን፣ በገጽ ብዛቱ 360 ሆኖ በከፍተኛ ጥራት ተመትሞ መዘጋጀቱ ታውቋል።
መጽሐፉ በይዘቱ ማህበራዊ፣ ስነ-ልቦናዊ እና አንደበተ-ርቱዕ የሆኑ የሕይወት እውነታዎችን በልብ አንጠልጣይ ትረካ የፈተሸ ጥልቅ የጥበብ ስራ እንደሆነ ተገልጿል።
Source: FastMereja









No comments yet.